Kene Gar ft. Mihiret Masresha Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2023
Lyrics
የፀሀዩን ብርሀን ሲሸፍን ደመና
በውስጤ ያለው ነውጥ እያደር ሲበዛ
አንደ ማንም አረ ሰው ነኝ ብዬ አልኩኝ
አይኖቼንም ወደ ሰማይ አነሳሁኝ
ታየኛለህ ወይ በትልቅ ባህር ውስጥ
የአለም ንፋስና ወጀብ ታንኳዬን ሲያናውጥ
ከእስትንፋሴ በላይ ቀርበህ ነው ያለኀው
የማልፍበትንም ነገር ሁሉ እያየህ ነው
ባይሰማኝም አንተ ሁሌ ከኔ ጋር ነህ
ብዙ ቃላቴ ማይገልፀውን ትሰማለህ
ብቻዬን አይደለሁም ከኔ ጋር ነህ
የምድር ላይ ጉዞ ማለት ደፋ ቀና
ልባቹን አዝሎት ጉልበትም ሲከዳ
ድካማችን እጅግ በዝቶ አላልቅም ሲል
አምላክ አለ ሸክማቹን ስጡኝ የሚል
ለኛ የከበደ ለእግዚአብሄር እጅግ ቀላል ነው
ባይመስለንም እንኳ እርሱ ሁሌ ከኛ ጋር ነው
ከኛ ጋር ነው