Yelib Amlak Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2023
Lyrics
ውጪዬን አግጬ
ለሰው ሁሉ ብታይ ለአይናቸው ደምቄ
ወሬዬን አክብጄ
ውስጤ ሳይፈልግህ ብዙ ባወራልህ
አምልኮን አድምቄ
ቤቴ ስገባ ግን ሙሾዬን ብገጥም
እጆቼን በአደባባይ ብዘረጋ
ምላሴ ውዳሴህን ቢያወራ
አንተ ጓዳዬን ትመለከታለህ
ከአንደበት የተሰበረን ልብ ታያለህ
ወደ ጓዳዬ ትመለከታለህ
በእውነት የተሰበረን ልብ ታያለህ
ቃላቴን ከሽኜ
ምንም ሳልታዘዝህ ብዙ ባወራልህ
በሰው ፊት ዘልዬ
ጉልበቴ ሳይንበረከክ ድርጊተን ባሳምርልክ
ጥበቤን ብናገር
ውብ አባባሌ አንተን አያስገርም
እጆቼን በአደባባይ ብዘረጋ
ምላሴ ውዳሴህን ቢያወራ
አንተ ጓዳዬን ትመለከታለህ
ከአንደበት የተሰበረን ልብ ታያለህ
ወደ ጓዳዬ ትመለከታለህ
በእውነት የተሰበረን ልብ ታያለህ
የልብ አምላክ ምንሰራው አይማርክህም
ልባችንን ግን ታያለህ