Destaye Neh ft. Exodus Getahun Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2023
Lyrics
ብዙ በሕይወቴ የሚሆነኝን ፈለኩ
የውስጤን ፍላጎት እርካታን ለማግኘት
ትርጉም ሚሰጠኝን አንድም ባላገኝም
አንተ ስላለኸኝ ምንም አይጎለኝም
የነገ ተስፋዬ የዛሬ አለኝታ
ፅኑ መደገፊያ የሕይወት እንጀራ
የመንገዴ ብርሃን በእውነት ምትመራኝ
አንተ ደስታዬ ነህ የሕይወቴ ቃና
የልቤ መዝሙር የነፍሴ ተድላ
አንተ ደስታዬ ነህ የሕይወቴ ቃና
የልቤ መዝሙር የነፍሴ ተድላ
የመንግሥትህ ሽታ ሲያውድ መአዛው
ደስታው የመንፈስ ቅዱስ ፅድቅና ሰላም ነው
ጠብቆኛል እጅህ ጉዞዬን እያቀና
በራልኝ መንገዴ የሕይወቴ ጎዳና
የነገ ተስፋዬ የዛሬ አለኝታ
ፅኑ መደገፊያ የሕይወት እንጀራ
የመንገዴ ብርሃን በእውነት ምትመራኝ
አንተ ደስታዬ ነህ የሕይወቴ ቃና
የልቤ መዝሙር የነፍሴ ተድላ
አንተ ደስታዬ ነህ የሕይወቴ ቃና
የልቤ መዝሙር የነፍሴ ተድላ
ምናጣሁ ምን ጎደለብኝ ሞልቶ ተርፎ ከእጅህ
ተፈልጎ መች ይታጣል አይከፋም ፊትህ
ደስ ይላል ያለመልማል መንፈስህ መገኘትህ
የልቤ መዝሙር ነህ ጌታ የሕይወቴ ደስታ
ምናጣሁ ምን ጎደለብኝ ሞልቶ ተርፎ ከእጅህ
ተፈልጎ መች ይታጣል አይከፋም ፊትህ
ደስ ይላል ያለመልማል መንፈስህ መገኘትህ
የልቤ መዝሙር ነህ ጌታ የሕይወቴ ደስታ
ምናጣሁ ምን ጎደለብኝ
ምናጣሁ ምን ጎደለብኝ ሞልቶ ተርፎ ከእጅህ
ተፈልጎ መች ይታጣል አይከፋም ፊትህ
ደስ ይላል ያለመልማል መንፈስህ መገኘትህ
የልቤ መዝሙር ነህ ጌታ የሕይወቴ ደስታ