Mihiretih Ayalkim Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2023
Lyrics
ስራችንን ሁሉ ታውቃለህ አንድም ሳይቀርህ
የየለት አካሄዳችንም ካንተ አይሰወርም
ሁላችን ሀጥያትን ሰርተናል ክብርህ ጎሎናል
በእግራችን ሚያቆመን ፀጋህም ሁሌ ያስፈልገናል
ፀሀይ ወጥታ እለክትገባ ምህረትህ አያልቅም
በለሊት ድቅድቅ ጨለማ ምህረትህ አያልቅም
ሀጥያታችን እጅግ ቢበዛ ምህረትህ አያልቅም
ተስፋ ባይታይም እንኳ ምህረትህ አያልቅም
በድካማችን ልታግዘን አንተ ሀያል ነህ
ስለ በደላችን ሞተሀል የኛን ቦታ ወስደህ
ፍቅርህን በኛ ላይ ስታፈስ ከቶ አትሰስትም
ዘወትር ታነፃናለህ በቅዱሱ ደምህ
ፀሀይ ወጥታ እለክትገባ ምህረትህ አያልቅም
በለሊት ድቅድቅ ጨለማ ምህረትህ አያልቅም
ሀጥያታችን እጅግ ቢበዛ ምህረትህ አያልቅም
ተስፋ ባይታይም እንኳ ምህረትህ አያልቅም
የምህረት አምላክ እኛን ወደድክና
ማቃችንን ቀደህ ፀጋን አለበስከን
የምህረት አምላክ እኛን ወደድክና
እዳችንን ከፍለህ ልጅህ አደረከን
ፀሀይ ወጥታ እለክትገባ ምህረትህ አያልቅም
በለሊት ድቅድቅ ጨለማ ምህረትህ አያልቅም
ሀጥያታችን እጅግ ቢበዛ ምህረትህ አያልቅም
ተስፋ ባይታይም እንኳ ምህረትህ አያልቅም