Lezelalem Amesgagn ft. Tensae Kunu Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2023
Lyrics
ኢየሱስ ወዳጄ የልቤ ጓደኛ
ከእስተንፋሴም ይልቅ ትቀርብና
ታዋየኛለህ የውስጤን ትርታ
አንተ አይተህ የማታውቀው የለምና
ብዙ ብዙ ብዙ ነው ውለታህ
ልዘረዝር ብሞክር ቃላት አይበቃ
በእኔ ላይ መዝሙር ዘመርክ አዎ ዘመርክ የፍቅርህን ቅኝት
እምባዬንም ሁሉ አበስክ እየሸሸግህ በሰፊው እቅፍህ
ሳላቋርጥ አወራለሁ ብዙ አለ ለእኔ ያደረከው
ለዘላለም አመስጋኝ ነኝ ምንም የለም ለእኔ ያልሆንክልኝ
ኢየሱስ አፅናኜ ምታረገኝ ቀና
ወጀቡ በዝቶ ኃይል ሲከዳኝ
ትራመዳለህ ከማዕበሉ በላይ
አንተን ሲያይህ ነውጥ ሁሉ ፀጥ ይላል
በእኔ ላይ መዝሙር ዘመርክ አዎ ዘመርክ የፍቅርህን ቅኝት
እምባዬንም ሁሉ አበስክ እየሸሸግህ በሰፊው እቅፍህ
ሳላቋርጥ አወራለሁ ብዙ አለ ለእኔ ያደረከው
ለዘላለም አመስጋኝ ነኝ ምንም የለም ለእኔ ያልሆንክልኝ
በኛ ላይ ትዘምራለህ
የፍቅርህን መዝሙር
ኢየሱስ ሰላሜ ፅኑ መደገፊያ
ከሚከበኝ ነውጥ ሁሉ መሸሸጊያ
የእውነት ጋሻዬ ከለላዬ አንተ ነህ
በክንፎችህ ጥላ ውስጥ አሳድረህ ታኖራለህ