Siladerekew Lawera Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2023
Lyrics
እኔስ ተመለከትኩ አየሁ የኋላዬን
ባሳለፍኩት ሁሉ ስትሄድ አብረኸኝ
እጅህ እየያዘኝ ስንቱን አሻገርከኝ
እረኛዬ ሆነህ በብዙ መራኸኝ
አባቴ እልሃለሁ ባንተ ሁሉን አልፌአለሁ
ስላደረከው ላውራ ምንም ቃላት ባይበቃ
ውለታህ እጅግ ብዙ ነው
ነፍሴም ሁሌም ተነሺ እግዚአብሔርን አስቢ
አዲስ ምስጋና ለእርሱ ሰዊ
አስታውሳለሁኝ ኃያል ክንድህን
ከክፉ ደብቆ ብርታት የሆነኝን
በጉያህ ሸሽገህ አለሁልህ አልከኝ
እየተከታተልክ ከክፋት አስጣልከኝ
አባቴ እልሃለሁ ባንተ ሁሉን አልፌአለሁ
ስላደረከው ላውራ ምንም ቃላት ባይበቃ
ውለታህ እጅግ ብዙ ነው
ነፍሴም ሁሌም ተነሺ እግዚአብሔርን አስቢ
አዲስ ምስጋና ለእርሱ ሰዊ