Tebekaleh Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2023
Lyrics
ብዙውን ተመኘሁ ትልቅ ፍላጎቴ
ይኼኛውን ብይዝ አያልቅም መሻቴ
ነገ ተነስቼ ለሌላው ብደክም
እለፋለሁ እንጂ መቼም አይሞላኝም
አንተ ትበቃለህ ብቻህን ታረካለህ
የምፈልገውን ሁሉ ባገኝ
በተራሮችም ላይ ባዶ ነኝ
ያላንተ ሁሉም ከንቱ ነው
እግዚአብሔር ብቻ ነው ሚሞላው
ፈጣሪዬ አንተ ነህ በእጅህ የሰራኸኝ
ከአፈር አበጅተህ እስትንፋስ ሰጠኸኝ
ሙላቴን ብፈልግ አንተ ሳትኖርበት
ባለም ያለው ሁሉ አይሞላም የኔን ጉድለት
አንተ ትበቃለህ ብቻህን ታረካለህ
የምፈልገውን ሁሉ ባገኝ
በተራሮችም ላይ ባዶ ነኝ
ያላንተ ሁሉም ከንቱ ነው
እግዚአብሔር ብቻ ነው ሚሞላው
አንተ ትበቃለህ ብቻህን ታረካለህ
የምፈልገውን ሁሉ ባገኝ
በተራሮችም ላይ ባዶ ነኝ
ያላንተ ሁሉም ከንቱ ነው
እግዚአብሔር ብቻ ነው ሚሞላው
ትበቃለህ