Yalkegnin Belibe Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2023
Lyrics
በልጅነት ነው አንተ የጠራኸኝ
ለልቤ ተናግረህ ቃልክን ያሰማኸኝ
መንገዴን ሁሉ እየሰራህልኝ
ኪዳንህን በእኔ ሕይወት አፀናህ
ሕያው ቃልህ ከቶ አይደክምም
ትተጋለህ እስከምትፈፅም
የማንንም እገዛ ሳትፈልግ
ትችላለህ ሁሉን ልታደርግ
ያልከኝን በልቤ ሰወርኩ
እንዳልታመን በሌላ
በእኔ አቅም አንዳች ላይሆን
አንተ ግን ድንቅን ልትሰራ
በጉዞ ላይ ነኝ ረጅሙን ጎዳና
እስከምደርስ ድረስ ወዳሰብከው ስፍራ
እንዴት እንደሆነ መንገዱን ባላውቅም
በእጅህ እስከሆንኩ ፈጽሞ አትጥለኝም
ሕያው ቃልህ ከቶ አይደክምም
ትተጋለህ እስከምትፈፅም
የማንንም እገዛ ሳትፈልግ
ትችላለህ ሁሉን ልታደርግ
ያልከኝን በልቤ ሰወርኩ
እንዳልታመን በሌላ
በእኔ አቅም አንዳች ላይሆን
አንተ ግን ድንቅን ልትሰራ
ሰማይና ምድርን መላወን ፍጥረት በሙሉ
ያጸና ኃያሉ ቃልህ ሕያውነው ከቶ አይደክምም
ያልከኝን በልቤ ሰወርኩ
እንዳልታመን በሌላ
በእኔ አቅም አንዳች ላይሆን
አንተ ግን ድንቅን ልትሰራ