Aserarhin Ayew Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2023
Lyrics
አሠራርህን አየሁ ከውስጤ ጨለማ
በእሳት አምድ መርተህ ይዘኸኝ ስትወጣ
ወደምድረበዳ እኔን ስትጠራ
እንክርዳዴን ገፈህ እንቁን ልታወጣ
አሠራርህን አየሁ ከውስጤ ጨለማ
በእሳት አምድ መርተህ ይዘኸኝ ስትወጣ
ወደምድረበዳ እኔን ስትጠራ
እንክርዳዴን ገፈህ እንቁን ልታወጣ
ይህን ያንን ነገሬን ስራልኝ ብዬ ስጠይቅህ
አንተ ሁሉን ችለህ ሳለህ እኔን ግን ልትሰራ ወደድህ
ከምትሰጠኝ ነገር ሁሉ በላይ
የኔ ዋጋ ለአንተ እጅግ ይበልጣል
ከእኔ በላይ ለእኔ ታማኝ ነህ
እጄን ይዘህ ልቤን ትመራለህ
አሠራርህን አየሁ ከውስጤ ጨለማ
በእሳት አምድ መርተህ ይዘኸኝ ስትወጣ
ወደምድረበዳ እኔን ስትጠራ
እንክርዳዴን ገፈህ እንቁን ልታወጣ
ብዙ መሆን ካለብኝ እራሴን ጎድዬ አገኛለሁ
የሆንኩትን ሰው በሙሉ አንዳች ሳይቀር ደግሞ አወከው
ከጎደለኝ ከሌለኝም በላይ
የማላውቀውን ሙላትህን እንዳይ
ወስደህ ራስህን በድንቅ ትገልጣለህ
እግዚአብሔር መልካም እረኛ ነህ
አሠራርህን አየሁ ከውስጤ ጨለማ
በእሳት አምድ መርተህ ይዘኸኝ ስትወጣ
ወደምድረበዳ እኔን ስትጠራ
እንክርዳዴን ገፈህ እንቁን ልታወጣ