Gize Lyrics
- Genre:Soul
- Year of Release:2024
Lyrics
አይ መታደል ወይ መስማማት
ይጋርዳል ካለም ክፋት
ውሎ ማደር መች ከበደው
ይዞን ማጣት ላለመደው
ጊዜ ጊዜ ጊዜ
የነበረው ህብትም
ድንገት ዛሬ ቢያከትም
ቢባክንም
እንዲ ነው ለካ ሲጨልም ተስፋ
ነዶ ሲያበቃ ብርሃን ሲጠፋ
ለመሬት ሲቀርብ ጉልበትም አልቆ
መተረማመስ ደስታን ተሰርቆ
አቤት ሲያዘናጋ ሲበዛ ምቾቱ
የጎደለ ለት ነው የሚያመው እውነቱ
የሚያብረቀርቀው መቼ ያዛልቃል
ህሊናን ያጣህ ቀን ዘላለም ያበቃል
አይ መታደል ወይ መስማማት
ይጋርዳል ካለም ክፋት
ውሎ ማደር መች ከበደው
ይዞን ማጣት ላለመደው
ጊዜ ጊዜ ጊዜ
የነበረው ህብትም
ድንገት ዛሬ ቢያከትም
ቢባክንም
የፈካው ደብዝዞ ሲዋጥ በጨለማ
ሲሰናከል ጉዞው ከያዘው አላማ
የኑሮ ፈተና ያኔ ነው ሚገባው
የዚች አለም እውነት በግልፅ የሚታየው
አይ መስማማት ወይ መታደል
ይጋርዳል ካለም በደል
ውሎ ማደር መች ከበደው
ይዞን ማጣት ላለመደው
ጊዜ ጊዜ ጊዜ
የነበረው ህብትም
ድንገት ዛሬ ቢያከትም
ቢባክንም
ጊዜ ጊዜ ጊዜ
ድንገት ዛሬ ቢያከትም
ቢባክንም
ጊዜ ጊዜ