
Lemiyalf Lyrics
- Genre:Soul
- Year of Release:2023
Lyrics
ቆይ ለምን ብዬ…ለሚያልፍ ቀን
እኮ ለምን ብዬ…ለሚያልፍ ቀን
መጨነቄን ተውኩት ይቅር
ለኔ ያልሆነው ይበል ጥንቅር
ዋናው ሰላም ነው ለቤቴ
ሁሌም አዲስ ነች ህይወቴ
ያስጨነቁኝ ሁሉ አልፈው አሁን ሳያቸው
ይገርመኛል ይደንቀኛል ሳስባቸው
ትላንት ነች ያዳነችኝ መድሀኒቴ
ዛሬ ቆሜ ስታዘባት ሙሉ ቤቴ
ለሚያልፍ ቀን... ለሚያልፍ ቀን...
ለሚያልፍ ቀን... ለሚያልፍ ቀን...
ተውኩት ተውኩት ይቅርብኝ
ከላይ አይሆንም ካለኝ
ይብቃ ዋናው ሰላሜ ነው
ይመጣል አይቀር ለኔ ያለው
የቻልኩት …እኔው ልሞክር
ያቃተኝን…ለሰው ላማክር
ተምርያለው ትግስትንም
ችሎ ማለፍ ፅናትንም
ቀን ለጣለው ይመጣል ቀን
ዛሬን ስናልፍ ነገን አይተን
ያስጨነቁኝ ሁሉ አልፈው አሁን ሳያቸው
ይገርመኛል ይደንቀኛል ሳስባቸው
ትላንት ነች ያዳነችኝ መድሀኒቴ
ዛሬ ቆሜ ስታዘባት ሙሉ ቤቴ
ለሚያልፍ ቀን... ለሚያልፍ ቀን...
ለሚያልፍ ቀን... ለሚያልፍ ቀን...
ተውኩት ተውኩት ይቅርብኝ
ከላይ አይሆንም ካለኝ
ይብቃ ዋናው ሰላሜ ነው
ይመጣል አይቀር ለኔ ያለው
ሁሉም ያልፋል ይነጋል አይቀርም ጨልሞ
ቀን ይመጣል ይነሳል ጉልበቴ ታክሞ
ሁሉም ያልፋል ይነጋል አይቀርም ጨልሞ
ቀን ይመጣል ይነሳል ጉልበቴ ታክሞ