
Betizeta Kerto Lyrics
- Genre:Soul
- Year of Release:2023
Lyrics
የኔ ፍቅር...የልቤ ጨረቃ
ኑርልኝ ሁሌም... ባትሆንም ከኔጋ
ደስታህን እመኛለው...ዘላለም ፈገግታህን
ከጄ ብታመልጥ እንኳን...ብንኖርም ተለያይተን
እሱ ካላለ አይሆንም...እኔም ተቀብዬዋለው
አብረን ባንሆን እንኳን...ጥሩ እመኝልሀለው
ውዴ
ሁሉ ቢቀር አለ ትዝታችን
ማይረሳ ውሎ ምሽታችን
ምናወራው ድብቅ ሚስጥራችን
ቀርቷል ተቆልፎ ከልባችን
ሁሉ ቢቀር አለ ትዝታችን
ማይረሳ ውሎ ምሽታችን
ምናወራው ድብቅ ሚስጥራችን
ቀርቷል ተቆልፎ ከልባችን
የኔ አለም...የደስታዬ አፍላቂ
ብፈልግ አጣሁ...የለህም ተተኪ
መለያየት ያለ ነው...እሱ ጠፍቶኝ አይደለም
ፍቅር መቶ ይሄዳል...ወዶ ያላጣ የለም
ሳስበው ግን ይከብዳል...መኖር ካላንተ ለኔ
እንዘልቃለን ብዬ ነበር...እስካለም ፍፃሜ
ውዴ
ሁሉ ቢቀር አለ ትዝታችን
ማይረሳ ውሎ ምሽታችን
ምናወራው ድብቅ ሚስጥራችን
ቀርቷል ተቆልፎ ከልባችን
ሁሉ ቢቀር አለ ትዝታችን
ማይረሳ ውሎ ምሽታችን
ምናወራው ድብቅ ሚስጥራችን
ቀርቷል ተቆልፎ ከልባችን
ደግሜ ባገኝህ ደስታዬ ልዩ ነው
ግን ሆነሃል የሌላ ሁሉም ለበጎ ነው
ቅር ቢያሰኘኝም አምኜበታለው
በል ደህና ሁንልኝ ሁሌም ወድሀለው
ደግሜ ባገኝህ ደስታዬ ልዩ ነው
ግን ሆነሃል የሌላ ሁሉም ለበጎ ነው
ቅር ቢያሰኘኝም አምኜበታለው
በል ደህና ሁንልኝ ሁሌም ወድሀለው
ውዴ....ውዴ
ሁሉ ቢቀር አለ ትዝታችን
ማይረሳ ውሎ ምሽታችን
ምናወራው ድብቅ ሚስጥራችን
ቀርቷል ተቆልፎ ከልባችን
ሁሉ ቢቀር አለ ትዝታችን
ማይረሳ ውሎ ምሽታችን
ምናወራው ድብቅ ሚስጥራችን
ቀርቷል ተቆልፎ ከልባችን