
Hiwot Lyrics
- Genre:Soul
- Year of Release:2023
Lyrics
አንተን...ብቻ ሳልም ኖሬ
ያላንተ ማን አለ ምክኒያት ለመኖሬ
ነህ አለሜ
አኔም...ከእቅፌ ላርግህ ከደረቴ
ያላንተ እኮ ከንቱ ነው ህይወቴ
ብትርዳኝ ውስጤን
ና...ቀረብ በል ወደኔ
ልሁን ከጎንህ እንተም ሁን ከጎኔ
የልብህን ትርታ ልስማው ልንራስ ከደረትህ ሁሌ
ፈዞ...ማየቱን አላረፈ አይኔ
የሌለህ እስኪመስል በአካል በውኔ
ሳይህ አሁንም እንዳዲስ ይደነግጣል ምስኪኑ ልቤ
አንተ እኮ ለኔ...ያለህ ንፁ ፍቅር
ደግነትህ ብዙ... ያሳየኸኝ ክብር
ባንተ ፈታሁት...የፍቅርን ሚስጥር
አንተን...አብዝቼ የማስበው
አላውቅም ካንተ ሌላ ሰው
ልቤም ያንተ ነው
ምን...ቢሆን ነው ግን ምክኒያቱ
ሁሌም የምታረገኝ ብርቱ
ኑሮ ፈተና ሲሆንብኝ ሲከብድብኝ መሰንበቱ
አንተ እኮ ለኔ...ያለህ ንፁ ፍቅር
ደግነትህ ብዙ... ያሳየኸኝ ክብር
ባንተ ፈታሁት...የፍቅርን ሚስጥር
ማነው ካንተ በላይ
እኔን አውቃለው ባይ
አሳየኸኝ ፍቅር
የህይወትን ሚስጥር