Minew Lyrics
- Genre:Soul
- Year of Release:2023
Lyrics
እኔ እንደው ያላንተ... መንፈሴ ባትረካ
ደረስኩኝ ከበርህ...ፍቅርህን ፍለጋ
አንተ ግን የለህም... ከደጅህ ብመጣ
ኩራቴን ደብቄ...ላወራህ በእርጋታ
የኔስ ልብ አልቻለም
ናፍቆቱ ገሎኛል
አለሁ በለኝ ውዴ
ማረገው ትፍቶኛል
ምነው...ምነው
ፍቅራችን በቃህ ወይ ምነው
ምነው...ምነው
ቃልኪዳናችንን ተውከው ምነው
መሰበሬን አይተህ...መተህ አቃናኸኝ
ቁስሌ ሳይበግርህ...አቅፈህ ተቀበልከኝ
ቃል እንደገባኸው...ስንገናኝ ያኔ
የተጎዳው ልቤን...ፈወስከው በቅኔ
ግን ከህመሜ ሳልድን ገና
ውስጤን አደማኸው
ሳቅህ መዳኒቴ ነበር
ባሰብኝ በምን ላክመው
ምነው...ምነው
ፍቅራችን በቃህ ወይ ምነው
ምነው...ምነው
ቃልኪዳናችንን ተውከው ምነው
ልቤን በምላስህ
ስጋዬንም ባይንህ
እስርስር አርገኸው
እንዳልተርፍ አድርገህ
ይኸው ግራ ገብቶኝ
ፍቅሬን ተቀምቼ
ሰው መሆን አቃተኝ
እራሴን አጥቼ
ምነው... ምነው... ምነው
ምነው... ምነው... ምነው
ምነው...ምነው
ፍቅራችን በቃህ ወይ ምነው