![Sew Hulu](https://source.boomplaymusic.com/group10/M00/11/06/971986f4020147b89a29f6755fe4a86f_464_464.jpg)
Sew Hulu Lyrics
- Genre:Soul
- Year of Release:2023
Lyrics
ሰው አክባሪ ፈሪ አምላኳን
ማንነቷም ከወርቅ ይበልጣል
ሰው መውደድን ታቅበታለች
ፍቅር መስጠትን ትችልበታለች
ልቧ ቅን ነው ክፋት አያውቃትም
ከራሷ ቀንሳ ሰጪ ነች ያላትን
እሱ ሲፈጥራት አርጏታል ሙሉ
አትጠገብም ላያት ሰው ሁሉ
ሰው…ሁሉ
ሰው…ሁሉ
አትደበቂ...ውጪ ታያቸው
ሁሉም ከቦሻል...አንድ በያቸው
ረቂቅ እንቁ ነሽ…ሁሉ ይመኝሻል
ብርቅዬ ፍጡር...አርጎ ሰርቶሻል
ይመኝሻል ይመኝሻል
ይመኝሻል ሰው ሁሉ ሰው ሁሉ
ይመኝሻል ያደንቅሻል
ይመኝሻል ሰው ሁሉ ሰው ሁሉ
የጥበቡን ሞገስ ሰቶሻል
በበረከት ተከበሻል
ግሩም ፍጥረት ልዪ ሰው ነሽ
ልብሽ ብርሀን ደማቅ ነው ውበትሽ
ሰው…ሁሉ
ሰው…ሁሉ
አትደበቂ...ውጪ ታያቸው
ሁሉም ከቦሻል...አንድ በያቸው
ረቂቅ እንቁ ነሽ…ሁሉ ይመኝሻል
ብርቅዬ ፍጡር...አርጎ ሰርቶሻል
ይመኝሻል ይመኝሻል
ይመኝሻል ሰው ሁሉ ሰው ሁሉ
ይመኝሻል ያደንቅሻል
ይመኝሻል ሰው ሁሉ ሰው ሁሉ
ይመኝሻል
ሰው ሁሉ ሰው ሁሉ
ያደንቁሻል
ይመኝሻል ይመኝሻል
ይመኝሻል ሰው ሁሉ ሰው ሁሉ
ይመኝሻል ያደንቅሻል
ይመኝሻል