![Kena](https://source.boomplaymusic.com/group10/M00/11/06/971986f4020147b89a29f6755fe4a86f_464_464.jpg)
Kena Lyrics
- Genre:Soul
- Year of Release:2023
Lyrics
አይታለች የውስጤን ደስታ
ፀሐይ ፈክታ ወጥታ
ሆናለች ደስተኛ ደምቃ
ለኛ ውብ ጨረቃ
ደስተኛ ስለኔ
ደስተኛ ናት ለኔ
በጠበኩት ጊዜ ቀርቶ
ባልጠበኩት ቀን ድንገት መጥቶ
ጉድለቴን ሞልቶ
ሳይ ፍቅርህ ፀንቶ
አልኩኝ ቀና ቀና
ደግሞ ለምስጋና
ቀና ቃል ሰቶኛል ሰላም
ቀና ህይወት ሰላም
ቀና አካል ሰቶኛል መልካም
ቀና መውደድ በጣም
ቀንቶኛል ሰቶኛል
ቀንቶኛል ሰቶኛል
ሰው ባለበት ሰው ተርቤ
ያጣሁ መስሎኝ ስንቱን አስቤ
አንተን ቀርቤ
ሆኜ እንደልቤ
ሳይህ አመሰገንኩ
በፍቅርህ ነገስኩ
የበዛ ፍቅር የበዛ መውደድ
የበዛ ደስታ የቀና መንገድ
ከላይ ነው እንጂ ከላይ ሲታደል
መች ሊገኝ ሰው በመታገል
የበዛ ፍቅር የበዛ መውደድ
የበዛ ደስታ የቀና መንገድ
ከላይ ነው እንጂ ከላይ ሲታደል