![lemin. (ለምን)](https://source.boomplaymusic.com/group10/M00/08/12/1f340711e0524c48bcb560b2538e4810H3000W3000_464_464.jpg)
lemin. (ለምን) Lyrics
- Genre:Pop
- Year of Release:2024
Lyrics
አንድ ሁለት ሶስት ብዬ
ችዬ የማልቆጥረው
ውለታ አለብኝ እኔ
ልከፍል የማልችለው
መተንፈሴ ሳያንሰኝ
ሰጥቶኝ የምጎርሰው
እሱም አልበቃ ብሎት
ስለኔ የሞተው
አንተ እያለህ
ለምን ሰጋለሁ
ሰላሜና ደስታዬ
አንተ ሆነ ሳለህ
እኔ አልፈራም
እኔ አልሰጋም
እኔ አልሰጋም
እኔ አልፈራም
አው!
ኑሮ ቢከፋም ቢሆን ጨለማ
ሰማይ ቢጠቁር ሆኖ ደመና
ፀሀይ ብትጠፋ በጉም ተሸፍና
አለኝ ለኔ ተስፋ አልሆንም መና
በደረቅ በረሐ የሚያዘንብ መና
ልቤን የጣልኩበት ሌላ የለምና
አይጥለኝ አይተወኝ ሁሌ ነው ከጎኔ
ጌታ ወዳጅ አባት እና መድህኔ
አለ ለኔ
የምታመንበት በዘመኔ
አዎ
የማያፍርብኝ
ስወድቅ የሚያነሳኝ የሚሳሳልኝ
አዎ
ውዴ የኔ ነው
እኔም ሆንኩኝ አሁን
ምንም ማልፈራ
እሱ እያለ
ከኔ ጋራ ሜዳ ይሆናል
ያ ትልቅ ተራራ
አንተ እያለህ
ለምን ሰጋለሁ
ሰላሜና ደስታዬ
አንተ ሆነ ሳለህ
እኔ አልፈራም
እኔ አልሰጋም
እኔ አልሰጋም
እኔ አልፈራም
አው!