
Etebekalehu (እጠብቃለሁ) Lyrics
- Genre:Folk
- Year of Release:2024
Lyrics
መቼ ይሁን ጊዜው
መጨረሻው
የምደርስበት
ወደ ማምሻው
ኑሮ ታከተኝ ከበደኝ
አስጠላኝ ውሎዬ አዳሬ አልተመቸኝ
ልብ ያወርዳል
እጅግ ያደክማል
የተስፋ ቢስ ህይወት
መቅበዝበዝ የበዛበት
ከቶ የሌለበት ውበት
መተንፈሴ ትርጉም የለው
ለኔ ካልሆነ ደስታ
ውስጤ ባዶ አይሞላው
በፍፁም የአለም እርካታ
ሰላም የለውም እረፍት
ሌትተቀን መንከራተት
ዕድሜን መጨረስ ነው
በከንቱ በማያልቅ የኑሮ ውጣ ውረድ
አይታየኝ
ምንም አይታየኝ
የህይወት ትርጉሙ ጠፋኝ
ከሚኖር በታች ነኝ
ለምትል ነፍስ አለ መልስ
አለም ራሷ ጠፊ እንኳን ስጦታዋ
አንፀባርቃ አትቀር
ይጠፋል ብርሀኗ ስትገባ ፀሐይዋ
መልስ አለ ገና ለተናቀ ለተገፋው
እንዲሁ አያልፍ እንዳመረረ እንደከፋው
እጠብቃለሁ
እጠብቃለሁ