Lenate (ለእናቴ) Lyrics
- Genre:Folk
- Year of Release:2024
Lyrics
ቀኔ ጨለመ በረታ
ሀዘኔ በዝቶ አጣው ደስታ
በኩለ ቀን ጠለቀች ፀሀዬ
ሳልሞቃት ሳልጠግባት እኔ
አሁንስ ናፈቀኝ ሀሩሩ
ምነው በመጣ ወበቁ
ብርዱ ከበደ ገና ካሁኑ
ታዛው ቀዝቅዞ በቁሩ
በምን አቅሜ
ችዬ ልረሳሽ አለሜ
በምን ጉልበቴ
አስችሎኝ ልርሳሽ እናቴ
በምን አቅሜ
ችዬ ልረሳሽ አለሜ
በምን ጉልበቴ
አስችሎኝ ልርሳሽ እናቴ
ባዶዬን ቀረው ኧረ እኔስ
አለኝ የምለውን አጥቼ
አሁንስ ምን ቀረኝ ከጆቼ
ማመንም ከበደኝ አይኖቼን
ምኑን ልያዝ የቱንስ ልጨብጥ
ግራ ቀኙንም ባየው
ባስስ ብፈልግ እታች እላይ
ማለቂያ የሌለው ሀዘን
ሆኗል መራራ ስቃይ
በምን አቅሜ
ችዬ ልረሳሽ አለሜ
በምን ጉልበቴ
አስችሎኝ ልርሳሽ እናቴ
በምን አቅሜ
ችዬ ልረሳሽ አለሜ
በምን ጉልበቴ
አስችሎኝ ልርሳሽ እናቴ