Basebgn Lyrics
- Genre:World Music/Folklore
- Year of Release:2023
Lyrics
ባሰብኝ
ያንቺን አላዉቅም የሚሰማሽን
ሌት ተቀን ንሯል የኔ
መላመድ መውደድ እያደረጀዉ
ላንቺዉ ተሰቷል ቀኔ
እኔን ባሰብኝ እኔ (3)
እኔን ባሰብኝ እኔ
ዘንድሮስ ወየሁ እኔ
እኔን ባሰብኝ እኔ
ተስኖት ልቤ ማመን እንግዳ ሆኖበታል
ዉድጄ እንዲህ ስታይ እኔን ማን ይገምታል
ባዶ ነዉ የያዝኩት ሰዉነት
ልቤ ዉስጥ አንቺ ሞልተሽበት
ወረት እንዳልለዉ ከረመ
ነገሬ በፍቅርሽ ታመመ
አሀ አሀሀ ታዉቆብኛል
አሀ አሀሀ ብሶብኛል
እኔን ባሰብኝ እኔ (3)
እኔን ባሰብኝ እኔ
ዘንድሮስ ወየሁ እኔ
እኔን ባሰብኝ እኔ
ድምፅሽን መስማት ሁሌ
አይን አይንሽን ማየት ነዉ
ልቤን ደስ እያሰኘ
ቀኔን ቀን የሚያደርገዉ
ምላሽ ባልጠብቅም ያንቺኑ
ስወድሽ ሁሌ በየቀኑ
ግን ፈራሁ ሰልችቶሽ በኋላ
መዉደዴን እንዳትይዉ ችላ
አሀ አሀሀ ከትላንቱ
አሀ አዎ ብሷል እቱ
እኔን ባሰብኝ እኔ (3)
እኔን ባሰብኝ እኔ
ዘንድሮስ ወየሁ እኔ
እኔን ባሰብኝ እኔ