Melke Beqagn Lyrics
- Genre:World Music/Folklore
- Year of Release:2023
Lyrics
መልኬ በቃኝ
መዋብም ማጌጥም ለራስ ነዉ
መልኬ በቃኝ ብሎ ኩራት ምንድነዉ
ምን ቢያምር ቁንጅና ቢደንቅ አላመል አይደምቅ
እንዲህ አሳምሮ በሰራሽ ፈጣሪ
ተዉቢያለሁ ብለሽ በመልክሽ አትኩሪ
እንኳንስ ቁንጅና የሚመኩበት
ማን አለሁኝ ብሎ ይቀራል ከሞት
በመልክሽ ተማርኮ ምን ቢወድሽ ልቤ
አመልሽ ካልገዛኝ ሳወራሽ ቀርቤ
በቁጅና ብቻ መች ፍቅር ይዘልቃል
ሰዉ ቀርቦ በዉበት በፀባይ ይርቃል
አዬ...እኔን አይመስለኝም
አዬ...መልክ ብቻ ቆንጆ
አመል ከሌለበት ያፈርስ የሎወይ ጎጆ (2)
ዉበትማ ቁንጅናማ ቢሞሸለጊዜዉ
ሞት አይደል ወይ ሚዜዉ (2)
ዉበትማ ቁንጅናማ ካላወቁበት
ያፈርስ የለወይ ቤት (2)
አዝማች (2)
ሁሉም ይቀየራል በጊዜ በወረት
ማን ይቀራል ብለሽ ስርክ እንዳማረበት
ሰአቱን ጠብቆ ይረግፋል አበባ
ቀን እንደሚጨልም ፀሀይ ስትገባ
በፍቅር ተዋዶ ሲኖር በዚህ ምድር
አመል አይደለም ወይ ከሰዉ የሚያሳድር
የወደደሽ ልቤን ተይበፍቅር አዝልቂዉ
እኮራለሁ ብለሽ ኋላ እንዳታርቂዉ
አዬ....አምሮ ጽጌረዳ
አዬ...ቢታደል ዉበትም
ከሌለዉ መአዛ ንብ አያርፍበትም
አዬ...በቁጅና ብቻ
አዬ...ተይ ፍቅርን አትለኪዉ
በፀባይሽ ማርከሽ ልቤን አንበርክኪዉ
ዉበትማ ቁንጅናማ ቢሞሸር ለጊዜዉ
ሞት አይደል ወይ ሚዜዉ (2)
ዉበትማ ቁንጅናማ ካላወቁበት
ያፈርስ የለወይ ቤት (2)