Yigermal Lyrics
- Genre:World Music/Folklore
- Year of Release:2023
Lyrics
ይገርማል
የማይሠለችሽ የማይሠለችሽ
ፍቅር እንከንሽ
እንዳትሠለቺ። እንዳትሠለቺ
የተፃፈልሽ
አንዳንዴም አመል አንዳንዴ ላፍታ
ይወጣል ክፉ። ገፍቶ ዝምታ
አይ ልብሽ ጓዳው አያቅ መንደድን
አልፎ ተጓዥ ነው። አጉል መንገድን
ባለም ያለው ነዋይ ጌጡን
ልብሽ ያልወደቀው ሢጥልብሽ አይኑን
አመልሽን የናት አድርጎ ሠራና
ሢቀናብሽ ለጉድ። አይቻለውና
እንዲያው ይገርማል እንዲያው ይደንቃል
እንዲያው ይገርማል ይደንቃል
እንዲያው ይገርማል መላው ነገርሽ
ቃል ተሽንፏል ለክብርሽ
አዝ
ቀኑ የሚያልፊ። የሚረታ
ያንቺ ግን ይለያል። አያውቅም ሽውታ
ድንገት ወለም ይላል ሢጓዙ ተማምነው
ወረት አያቅሽም ተፈጥሮሽ ድንቅ ነው
እንደው ይገርማል። እንደው ይደንቃል
እንደው ይገርማል ይደንቃል
እንዲያው ይገርማል መላው ነገርሽ
ቃል ተሽንፏል ለክብርሽ
ይገርማል ይደንቃል በጣም
ይገርማል ይደንቃል
ተፈጥሮሽ ልዩ ነዉ በጣም ይገርማል