Endalemetadel Lyrics
- Genre:World Music/Folklore
- Year of Release:2023
Lyrics
እንዳለመታደል
እንዳለመታዳል ታደልኩሽ
አብረሺኝ ሳትሆኝ አፈቀርኩሽ
ባይኔ እንደሞሸርኩሽ ሆዴ /ተሞሸርኩሽ
ባይኔ እየሞሸርኩሽ /እንደሞሸርኩሽ
ኡ ፍቅርሽ ታላቅ ሆነች ሲበዛ
ተማረከች ነፍሴ እንደዋዛ
ኡ ሰሰትኩሽ ዉስጤ ደነገጠ
እኔነቴ እንደሰም ቀለጠ
በፍቅርሽ ዉቂያኖስ ሰመጠ
አፍቅሮ መፈቀር ናፈቀኝ
የፍቅር እርሀብ ዉስጤን ወረሰኝ
ሀዘኔ በረከተ በዛ ፍቅሬ አታ
ኑሮ ጣእም ለዛ
ስንት አመት ልዉደድሽ ታዲያ
አንቺ የፍቅሬ መጠጊያ
እንዳለመታዳል ታደልኩሽ
አብረሺኝ ሳትሆኝ አፈቀርኩሽ
ባይኔ እንደሞሸርኩሽ ሆዴ /ተሞሸርኩሽ
ባይኔ እየሞሸርኩሽ /እንደሞሸርኩሽ
ኡ የፍቅር ዜማ ነሽ ሚስጥር
ድንቅ አርጎሽ የዉበት ደምስር
ኡ አንቺ የፍቅር እርሀብ ሚስጥሬ
ድብቅ የዉስጥ ህመም ስቃዬ
ናፈቀኝ የአፍ መፍቻ ቋንቋዬ
ኑሮ ባህር ከፍላ እንደሙሴ
አሻግራሽ ሳቅ እርቧት ጥርሴ
ዝም ብሎ ናፈቅሺኝ እንዲሁ
ይብላኝ ያንቺስ አንጀት ፅናቱ
ስንትአመት ልዉደድሽ ታዲያ
አንቺ የፍቅሬ መጠጊያ
ስንት አመት ልክሳልሽ ታዲያ
ፍቅርን ስል ፍቅርን ፍለጋ