
Sitina Lyrics
- Genre:Afrobeats
- Year of Release:2024
Lyrics
የመውደድሽ መጠን የማፍቀርሽ ጥልቁ ስጦታ
ባይለካም ጥጉ በዚህች ዓለም ስፍር ውለታ
ግና በገባኝ ልክ ልበልሽ ልናገር
አዎ ያርገው ለኔ ያንቺን ክፉ ነገር
ያ ሲቲና ያ ሲቲና
ያ ሲቲና ያ ሲቲና
መልከ ፀሐይ ልበ ቀና
ውብ ገር ገላ የት አለና
ለካ ስንለያይ እንዲህ ለካ በናፍቆት ያባባኝ
ለካ እኔኑ ነበረ ለካ ተፈጥሮሽ ያልገባኝ
ለካ አሁንማ አወኩት ለካ መች ያጠያይቃል
ለካ አዛኝነትሽን ለካ ሳር ቅጠሉ ያውቃል
ግና በገባኝ ልክ ልበልሽ ልናገር
አዎ ያርገው ለኔ ያንቺን ክፉ ነገር
ያ ሲቲና ያ ሲቲና
ያ ሲቲና ያ ሲቲና
መልከ ፀሐይ ልበ ቀና
ውብ ገር ገላስ የት አለና
ለካ ደጋግሞ ከልብሽ ለካ ፍቅር የማይነጥፈው
ለካ ለኔ ማማር ነበር ለካ ወዝሽ የረገፈው
ለካ እንደዋዛ ያዩት ለካ ንጥር ሰው አቅሙ
ለካ ከእጅ የወጣ እለት ነው ለካ የሚገባው ጥቅሙ
ግና በገባኝ ልክ ልበልሽ ልናገር
አዎ ያርገው ለኔ ያንቺን ክፉ ነገር
ያ ሲቲና ያ ሲቲና
ያ ሲቲና ያ ሲቲና
መልከ ፀሐይ ልበ ቀና
ውብ ገር ገላስ የት አለና
መቼም መቼም መቼም ቢሆን
ደሞ እንዳንቺ ማንስ ሊሆን
ካለሽበት ጠዋት ማታ
ያብዛው ያንቺን ሰላም ደስታ
ለፍቅር ሲቲና ለመውደድ ሲቲና
ከራሱ ቀንሶ ማን ኖረልኝ እና
እንደ እህት ሲቲና እንደ እናት
ከራስ በላይ መኖር ታድለሻል እና