
Leyelegn Lyrics
- Genre:Afrobeats
- Year of Release:2024
Lyrics
ከአንድ ሕይወቴ በላይ ከራሴ አስበልጬ
ብወዳት ብወዳት ቆሜ ተቀምጬ
አላሳርፍ አለኝ ልቤ አትሮኖሷ
እየኖረ በኔ እያደላ ለሷ
አሻፈረኝ አለ ሆዴም አመረረ
ወጣ ስትል ገና እየጠረጠረ
እንደፈራሁት ለየልኝ
እንጃ የኔንስ ለጤና ያድርግልኝ
ልቤን አልሰጥም ለሰው ብዬ ኖሬ ኖሬ
ስል ኖሬ ፎክሬ
ወበከንቱነቴንም ይለይለት ብላ አ ሀ ሀ
አሳየቺኝ ችላ
እንደፈራሁት ለየልኝ
እንጃ የኔንስ ለጤና ያድርግልኝ
እኔስ ለየልኝ
ኧረ ለየልኝ
እናት የጠፋው
ልጅ አደረገኝ
እኔስ ለየልኝ
ኧረ ለየልኝ
እናት የጠፋው
ልጅ አደረገኝ
መኖር እማ ዛሬም አለው ዛሬም አለው
ግን በጠና ተይዣለው ተይዣለው
እኔስ ለየልኝ
ኧረ ለየልኝ
እናት የጠፋው
ልጅ አደረገኝ
እኔስ ለየልኝ
ኧረ ለየልኝ
እናት የጠፋው
ልጅ አደረገኝ
ከአንድ ሕይወቴ በላይ ከራሴ አስበልጬ
ብወዳት ብወዳት ቆሜ ተቀምጬ
አላሳርፍ አለኝ ልቤ አትሮኖሷ
እየኖረ በኔ እያደላ ለሷ
አሻፈረኝ አለ ሆዴም አመረረ
ወጣ ስትል ገና እየጠረጠረ
እንደፈራሁት ለየልኝ
እንጃ የኔንስ ለጤና ያድርግልኝ
ክተት እንደተባለ ጦር ፍቅሯ ተጠራርቶ
በአንዱ በኔ ዘምቶ
አቤት ወዴት ብቻ ነው ቀን ከሌት ታጥቄ
አ ሀ ሀ ትህዛዟን ጠብቄ
እንደፈራሁት ለየልኝ
እንጃ የኔንስ ለጤና ያድርግልኝ
እኔስ ለየልኝ
ኧረ ለየልኝ
እናት የጠፋው
ልጅ አደረገኝ
ወዳጅ እማ ያም ያም አለው
ሁሉም አለው
ይብላኝ ፍቅር ላልታደለው
ላልታደለው
እኔስ ለየልኝ
ኧረ ለየልኝ
እናት የጠፋው
ልጅ አደረገኝ
እኔስ ለየልኝ
ኧረ ለየልኝ
እናት የጠፋው
ልጅ አደረገኝ