
Musheraye Lyrics
- Genre:Afrobeats
- Year of Release:2024
Lyrics
ይህው ዛሬ ላይ ቆሜ
አየሁ ተሳክቶልኝ ህልሜ
የተመኘሁት በዓለም
ለሕይወት መድመቂያ ቀለም
አንቺን ሰጠኝ አምላክ ከላይ
የለመኑትን የሚያይ
የዘመን ጌጤ አበባ
ፍቅርሽ ከቤቴ ከባ
ከአሰብኩበት ለመድረስ በዓይኖቼ እያየሁ
አረፈልኝ ሀሳቤ ፅዋዬንም ባንቺው ሞላሁ
ለክብር አብቅቶኛል ከዙፋኑ ፍቅርሽ ፍቅሬ
ትላንት የጎደለኝን ሞልቶ ዛሬ
ሙሽራዬ ሙሽራዬ
የሰርክ መድመቂያዬ
ሙሽራዬ ሙሽራዬ
የሰርክ መድመቂያዬ
…
ይህው ዛሬ ላይ ቆሜ
አየሁ ተሳክቶልኝ ህልሜ
የተመኘሁት በዓለም
ለሕይወት መድመቂያ ቀለም
አንቺን ሰጠኝ አምላክ ከላይ
የለመኑትን የሚያይ
የዘመን ጌጤ አበባ
ፍቅርሽ ከቤቴ ገባ
የዘወትር ውዳሴ ፀሎቴ እንጉርጉሮዬ
ከወይኑ ጠጅ አጠጣኝ በፍቅርሽ እድል ፋንታዬ
ዓለሙን አስረስቶ በራሱ ዓለም ለከተተኝ
ለፍቅርሽ መንኛለው ላሳረፈኝ
ሙሽራዬ ሙሽራዬ
የሰርክ መድመቂያዬ
ሙሽራዬ ሙሽራዬ
የሰርክ መድመቂያዬ