
Ney Ney Emamaye Lyrics
- Genre:Afrobeats
- Year of Release:2024
Lyrics
በቀናት ድግግም በአመታት ቆይታ
አያውቅም ቀንሶ የልብሽ እውነታ
ያንቺስ ፍቅር ይገርማል ይገርማል
ውሎ እያደር ይጥማል ይጥማል
ያንቺስ ፍቅር ይገርማል
ውሎ እያደር ይጥማል ይጥማል
አደን ሰምሮለት እንደቀናው ሰው ግዳይ
ይለኛል ደስ ደስ መልኬ ፊትሽ ላይ ሲታይ
ከዓይኔ መቅደስ የምትፈልቂ የደስታ እንባ ጠብታዬ
የልቤ ስር ብርታቴ ነሽ የድል አርማ ስጦታዬ
ነይ ነይ እማማዬ
ነይ ነይ እማማዬ
ነይ ነይ እማማዬ
ነይ ነይ እማማዬ
ሰው ቢለካ በፀባይ በለት እለት አኗኗር በምግባሩ
ሚዛን ደፍቶ ባህሪሽ አስመስክሯል ያንስሻል መከበሩ
በካህናት ሽብሻቦ በዲያቆናት ዝማሬ ቃል ውዳሴ
የተቃኘሽ የሕይወት እርካታ ነሽ ለአካልም ለመንፈሴ
ነይ ነይ እማማዬ
ነይ ነይ እማማዬ
ነይ ነይ እማማዬ
ነይ ነይ እማማዬ
በቀናት ድግግም በአመታት ቆይታ
አያውቅም ቀንሶ የልብሽ እውነታ
ያንቺስ ፍቅር ይገርማል ይገርማል
ውሎ እያደር ይጥማል ይጥማል
ያንቻስ ፍቅር ይገርማል
ውሎ እያደር ይጥማል ይጥማል
አደን ሰምሮለት እንደቀናው ሰው ግዳይ
ይለኛል ደስ ደስ መልኬ ፊትሽ ላይ ሲታይ
ካይኔ መቅደስ የምትፈልቂ የደስታ እንባ ጠብታዬ
የልቤ ስር ብርታቴ ነሽ የድል አርማ ስጦታዬ
ነይ ነይ እማማዬ
ነይ ነይ እማማዬ
ነይ ነይ እማማዬ
ነይ ነይ እማማዬ
ከዓይኖችሽ ላይ ብርሀን ከፊትሽ ገፅ ውበትን ተለዋውጣ
በፈገግታሽ ትለምልም በይ ሳቂልኝ ከደስታሽ ጀንበር ትውጣ
አሀዱ ብል ቀዳማይ እንከን አልባ ውብ ጠረን መአዛዬ
ስመ ጥሩ ምሳሌ ጅማሬ ነሽ ፍፃሜም የደስታዬ
ነይ ነይ እማማዬ
ነይ ነይ እማማዬ
ነይ ነይ እማማዬ
ነይ ነይ እማማዬ