Abetu Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2022
Lyrics
አቤቱ
መልካም መሬት ላይ ያረፈው ዘር
ወፎች አይለቅሙትም ወድቆ መንገድ ዳር
ከቶ አይጠወልግም በፀሀይ ሀሩሩ
ጠሊቅ መሰረቱ ህያው ቃልህ ዘሩ
አቤቱ
ከቶ ሳላቋርጥ እንዳፈራ ፍሬን
ቃልህ ይስበርልኝ የልብ መዝጊያዬን
አቤቱ
ለመንፈሴ እንዳድር ፈቃዴን ቸል ብዬ
ትምርትህ ይውረሰው ግብዙ እኔነቴን
አቤቱ
ቃልህን ማድመጤ ወደ ውስጤ ይለፍ
አዕምሮና ልቤም ከዓለም ሀሳብ ይትረፍ
ማዕበል ወጀቡን የስጋን ፈተና
ተሻግሬ እንድቆም ዕምነቴ እንድፀና
አቤቱ
ከቶ ሳላቋርጥ እንዳፈራ ፍሬን
ቃልህ ይስበርልኝ የልብ መዝጊያዬን
አቤቱ
ለመንፈሴ እንዳድር ፈቃዴን ቸል ብዬ
ትምርትህ ይውረሰው ግብዙ እኔነቴን
አቤቱ
መስማትን ሰምቼ ግን ካላስተዋልኩኝ
ማየቱን ችዬበት ካልተመለከትኩኝ
የተዘራብኝ ዘር እንዴት ስር ይሰዳል
እሾህ ማነቅ እንጂ ማስዋብ ከየት ያውቃል
አቤቱ
ከቶ ሳላቋርጥ እንዳፈራ ፍሬን
ቃልህ ይስበርልኝ የልብ መዝጊያዬን
አቤቱ
ለመንፈሴ እንዳድር ፈቃዴን ቸል ብዬ
ትምርትህ ይውረሰው ግብዙ እኔነቴን
አቤቱ