Tsadik Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2022
Lyrics
ጻድቅ
በሆነው ነገር ላይ በተከናወነው
ገናም ሊሆን ባለው ግዜ በሚገልጠው
እግዚአብሔር ጻድቅ ነህ ሁሉንም አዋቂ
ስራህ ትክክል ነው ቢበዛም ጠያቂ
የጠየኩህ ባይሆን የጠበኩት ቢቀር
እኔ ያመንኩህ ለክፋውም ቀን ጭምር
መንገድህ ቀና ስራህም ግሩም
የእውነት አምላክ ሀሳብህ ፍፁም
ጻድቅ ጻድቅ ጻድቅ ነህ አትሳሳትም ሁሌም ልክ ነህ
ጻድቅ ጻድቅ ጻድቅ ነህ አትታረምም ሁሌም ልክ ነህ
አይስት አንደበቴ ክፉ አይወጣው ከቶ
ይዘክራል እንጂ ማዳንህን አብዝቶ
የተደረገልኝ እልፍ ነውና
ከምሬት ይልቅ ብዙ ምስጋና
አይስት አንደበቴ ክፉ አይወጣው ከቶ
ይዘክራል እንጂ ማዳንህን አብዝቶ
የተደረገልኝ እልፍ ነውና
ከምሬት ይልቅ ብዙ ምስጋና
ጻድቅ ጻድቅ ጻድቅ ነህ አትሳሳትም ሁሌም ልክ ነህ
ጻድቅ ጻድቅ ጻድቅ ነህ አትታረምም ሁሌም ልክ ነህ
ጻድቅ ጻድቅ ጻድቅ ነህ አትሳሳትም ሁሌም ልክ ነህ
ተዘርግተው አሉ እጆችህ ለእኔ
ሊይዙኝ አጥበቀው በደስታም በሀዘኔ
ከስብራቴ ስር ብኖርም ጠፍቼ
ፍቅርህ ጠግኖኛል ከፊትህ መጥቼ ከፊትህ መጥቼ