Yihm Yansihal Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2022
Lyrics
ይሄም ያንስሃል
የምሥጋናችን አክሊል ይኸው በፊትህ
መቅደስህ ተሞልቷልና በመንፈስህ
ካህናቱም አንተን ያክብሩ
ላንተ ይቀኙልህ
በምሥጋና ይዘምሩልህ
ሰገነት ላይ በኅብረት ቆመው
ለክብርህ ይቀኙ ባንድነት ሆነው
የምሥጋናችን አክሊል ይኸው በፊትህ
መቅደስህ ተሞልቷልና በመንፈስህ
ካህናቱም አንተን ያክብሩ
ሹማምንት ሁልጊዜ ይገዙልህ ባሪያ ሆነው
ተንበርክከው
የጌቶች ጌታ ኃያል ለሆንከው
ያጎንብሱ ላንተ ዝቅ ብለው
ክብር ይስጡህ ላንተ ፊትህ ሰግደው
ያጎንብሱ ላንተ ዝቅ ብለው
ክብር ይስጡህ ላንተ ፊትህ ሰግደው
ላንተ ይቀኙልህ
በምሥጋና ይዘምሩልህ
ሰገነት ላይ በኅብረት ቆመው
ለክብርህ ይቀኙ ባንድነት ሆነው
ነገሥታት ከዙፋን ይነሡልህ ሊያወድሱህ በምሥጋና
አንተ በሥራህ ታላቅ ነህና
በማስተዋል ማን ይጠጋሀል
በጥበብስ ማን ይመስልሃል
ስምህ ኃያል ትልቅ ግሩም ነውና
የለህም ፍጹም አንተን መሣይ ዕኩያ
እግዚሀብሄር ይሄም ያንስሃል
ክብር ሁሉ ላንተ ይገባል
ማን ይመስልሃል
ብርሃን ተላብሰሃል
ዙፋናት ይሰግዳሉ
አንተ ጌታችን ነህ ይላሉ
ማን ይመስልሃል
ብርሃን ተላብሰሃል
ዙፋናት ይሰግዳሉ
አንተ ጌታችን ነህ ይላሉ