![Filega](https://source.boomplaymusic.com/group10/M00/08/17/77aa9920abd14385b62c353cb46ca27cH3000W3000_464_464.jpg)
Filega Lyrics
- Genre:Reggae
- Year of Release:2024
Lyrics
ወጣሁ ወረድኩልሽ ኩታበር ገራዶ
አይጨበጥ ነፋስ ልቤ አንቺን ወዶ
ወዴት ነሽ ጀግንዬ ኮምቦልቻ ነሽ ደሴ
መርሳ ነሽ ወልዲያ ቦረና ከሚሴ
የሠርክ ርኃቤ የሁልጊዜ ጥሜ
እቅፍሽ ውስጥ ኾኜ የሚሞቀው ደሜ
አብረውሽ የት ኼዱ
ውርጭ ኹኗል ዙሪያዬ ሊገድለኝ ነው ብርዱ
መታመሜን አይተው ባቲ ወረኢሉ
መርሳና ውርጌሳ ትሞታለህ አሉ
እኔ ግን አልሞትም መውደድ ያጸናኛል
መታመን አክሞ ፍቅር ያኖረኛል
አንቺ ሆዬ ለኔ ባቲ ያዘልቀኛል
አሀሀሀሀሀሀ ኦሆሆሆሆሆ
እኽል ውኃ ተውኩኝ መብል ምን ሊረዳኝ
አንቺን በማጣቴ የፍቅር ፆም ጎዳኝ
ደሴን ደጅ ጠናሁ ሐይቅ ዳር ቁጭ ብዬ
በትዝታሽ ሐረግ ልቤን አንጠልጥዬ
አምባሰል ዳመነ ገራዶ እያካፋ
አድራለሁ ሳስብሽ ሆዴ እየተከፋ
አይነጋልኝ ሌቱ ቀን አልመሽ ይለኛል
ይህን ያንቺን ፍቅር ማን ሰው ያስጥለኛል
መታመሜን አይተው ባቲ ወረኢሉ
መርሳና ውርጌሳ ትሞታለህ አሉ
እኔ ግን አልሞትም መውደድ ያጸናኛል
መታመን አክሞ ፍቅር ያኖረኛል
አንቺ ሆዬ ለኔ ባቲ ያዘልቀኛል
አሀሀሀሀሀሀ ኦሆሆሆሆሆ