![Teyim](https://source.boomplaymusic.com/group10/M00/08/17/77aa9920abd14385b62c353cb46ca27cH3000W3000_464_464.jpg)
Teyim Lyrics
- Genre:Reggae
- Year of Release:2024
Lyrics
የመስከረም ዐደይ - የበጋ ጨረቃ
መዉደድሽ አለልኝ - እኔ አልሞትም በቃ
እንኳን ኖረሽልኝ - ደስ እያሰኘሽኝ
ስቀሽ እያከምሽኝ - አቅፈሽ እያደስሽኝ
ካንቺ ጋራ መሆን - በምናብ ሽርሽር
መፍተሄ ስቃይ ነዉ - ሕምን የሚሽር
የኔ ጠይም ውበት - የኔ ጠይም ዓለም
የኔ ጠይም ዕጣ - የኔ ጠይም ቀለም
የኔ ጠይም ውበት - የኔ ጠይም ዓለም
የኔ ጠይም ዕጣ - የኔ ጠይም ቀለም
ለዓለም ማስታወሻ - ከነፍስ ጋ እሚያርግ
ትህትናሽ ዕጣ ነው - ለጽድቅ የሚዳርግ
አንዴ ወደ ናፍቆት - አንዴ ወደ ትዝታ
ሳይሆን በትካዜ - ሲሆን በፈገግታ
ባሳብ ወዲያ ወዲህ - እመላለሳለሁ
አንቺን በልቤ ውስጥ - በደግ አቆያለሁ
የኔ ጠይም ውበት - የኔ ጠይም ዓለም
የኔ ጠይም ዕጣ - የኔ ጠይም ቀለም
የኔ ጠይም ውበት - የኔ ጠይም ዓለም
የኔ ጠይም ዕጣ - የኔ ጠይም ቀለም
ምን ያህል ባምንሽ ነዉ - ምን ያህል ብወድሽ
ሆዴ ባዶ እስኪቀር - ሁሉን የምነግርሽ
ናፍቆት ኩረፊያ ንዴት - ተስፋ እርቅ ደስታ
ስዉ ታደርጊኛለሽ - ከስር የተፈታ
የኔ ጠይም ውበት - የኔ ጠይም ዓለም
የኔ ጠይም ዕጣ - የኔ ጠይም ቀለም
የኔ ጠይም ውበት - የኔ ጠይም ዓለም
የኔ ጠይም ዕጣ - የኔ ጠይም ቀለም
የኔ ጠይም ውበት - የኔ ጠይም ዓለም
የኔ ጠይም ዕጣ - የኔ ጠይም ቀለም
የኔ ጠይም ውበት - የኔ ጠይም ዓለም
የኔ ጠይም ዕጣ - የኔ ጠይም ቀለም