Tisegiyalesh Lyrics
- Genre:Reggae
- Year of Release:2024
Lyrics
አይወደኝም ብለሽ ትሰጊያለሽ አሉ
አንቺ አይደለሽ እንዴ ነገሬ በሙሉ
መና መኻል ረኃብ ውኃ መኻል ጥሜ
እንዳለ ይሰማኛል ስምሽ መኻል ስሜ
አይወደኝም ብለሽ ትሰጊያለሽ አሉ
አንቺ አይደለሽ እንዴ ነገሬ በሙሉ
መና መኻል ረኃብ ውኃ መኻል ጥሜ
እንዳለ ይሰማኛል ስምሽ መኻል ስሜ
ማን ኾነና ታዲያ የጎጆዬ ማሾ
የኑሮዬ ቅመም የህይወት ጣዕም እርሾ
አወይ መታደሌ ልቤ አንቺን ወዷል
እንዴት በዓይን እና ባገር ይቀለዳል?
አይወደኝም ብለሽ ትሰጊያለሽ አሉ
አንቺ አይደለሽ እንዴ ነገሬ በሙሉ
መና መኻል ረኃብ ውኃ መኻል ጥሜ
እንዳለ ይሰማኛል ስምሽ መኻል ስሜ
ምን ይሉት አባባል አይወደኝም ማለት
አንቺ ማለት ለኔ ሀሴት ዓለም ገነት
ብትሰምር ሕይወቴ ብደነቅ ቢያምርብኝ
አንቺን ብወድ ነው ሌላ ባልኩ ይቅርብኝ ሆ
ታዛዬ ጥላዬ አርፋለሁ ባንቺ ሥር
ልብሽ አምኖ ይረፍ ግድ የለም አይጠርጥር
እወድሻለሁኝ ይሄዉ ነዉ የኔ ቃል
ፍቅርሽ እንደ ጸበል ከራስ የሚያስታርቅ
አይወደኝም ብለሽ ትሰጊያለሽ አሉ
አንቺ አይደለሽ እንዴ ነገሬ በሙሉ
መና መኻል ረኃብ ውኃ መኻል ጥሜ
እንዳለ ይሰማኛል ስምሽ መኻል ስሜ