Chapter 6 : Alkerem Lyrics
- Genre:Alternative
- Year of Release:2024
Lyrics
ቢጠቁር ሰማዩ ውሃ አዝሎ ደመና
መብረቁ ቢያስፈራራኝ አልፌ እንዳልመጣ
ያኔ በልጅነት ቃል እንደገባሁኝ
እደርስልሻለው ባረፍድም ጠብቂኝ
ዝናቡ አካፍቶ ልብሴን ቢያበሰብስ
መሬቱ ጨቅይቶ እግሬን ቢያልፈሰፍስ
አልቀርም አልቀርም
እመጣለው ባረፍድም
የወንዙ ሙላት መንገዴን ቢዘጋው
የዶፉ ውሽንፍር ልቤንም ቢያሰጋው
አሁን አድጌአለው ጠብቂኝ ዉዴ
መድረሴ አይቀርም ባይቀናም መንገዴ
ዝናቡ አካፍቶ ልብሴን ቢያበሰብስ
መሬቱ ጨቅይቶ እግሬን ቢያልፈሰፍስ
አልቀርም አልቀርም
እመጣለው ባረፍድም
በለጋ እድሜዬ ፍቅርን ተምሬአለው
መስዋትነትንም ካንቺ አይቻለሁ
ለመንገድ የያዝኩት ሌላ ስንቅ የለኝም
የፈተናው ጉልበት ካንቺ አያስቀረኝም
ዝናቡ አካፍቶ ልብሴን ቢያበሰብስ
መሬቱ ጨቅይቶ እግሬን ቢያልፈሰፍስ
አልቀርም አልቀርም
እመጣለው ባረፍድም