
Chapter 1 : Hiwot Lyrics
- Genre:Alternative
- Year of Release:2024
Lyrics
ሰገንት ላይ ሆኜ አየኋት ስትጓዝ
ሰዎች ከበዋታል ቢሆምን ለየሗት
ቀርቤ እንዳላወራት ፈላጊዋ በዝቷል
ቸልም እንዳልላት ውበቷ ይጣራል
ወረድኩና ተከተልኩኝ ቀልቤን ጥዬ ነጎድኩ
ከሚያጋፉት ተጋፍቼ ከሚሮጡት ጋር እሮጥኩ
አይኔን አነሳው ላየት እንደገና
ግን አትታይም ግርግር ውስጥ ሆና
ይዛ ትሄዳለች መንጋውን አስከትላ
ወንዙን አቋረጠች ድምበሩን ተሻግራ
ወጣች ወረደች ዳገት ቁልቁለቱን
ይዛው ጠፋች የሚከተለውን
ፍላፃ ጉበትን አልፎ እስኪወጋ
የሚያስተውል የለም ሊታረድ ሲነዳ
ደርሶ መባቻዋ ወገግ ብትል ጨረቃዋ ሞልታ
የሰሜኑ ኮከብ ቢታየኝ ሲወጣ
ጎጆዬ ትዝ አለኝ መሽቶብኛል ለካ
ጎጆዬ ትዝ አለኝ መሽቶብኛል ለካ
"ማን ትሆን?" አልኳቸው ስሟን እንዲነግሩኝ
ልመለስ አስቤ እየተሰናዳሁኝ
በአግራሞት አዩኝ ጥያቄው ደንቋቸው
አለማወቄን አየሁኝ ከዓይናቸው
"ሕይወት ናት!" አለኝ አንዱ በድፍረት
መልስ አገኝ ብሎ እዲሆነኝ እረፍት
ድምፁ ሰነጠቀኝ ባዶነት ተሰማኝ
እንደከሰርኩ አወኩ እንደጠፋው ገባኝ
ፍቅሬን የኔን ውድ እዛ ማዶ ጥዬ
እዚህ ድረስ መጣሁ ውበት ተከትዬ
መንፈሴ ቢታወር በስጋ ተታለልኩ
ከአይምሮ ብጎድል ህይወት በሞት ቀየርኩ
እንግዲ ልመለስ እዚህ ምንም የለኝ
ጎጆዬ ይሻለኛል ፅዮን እርስት አለኝ
እንግዲ ልመለስ እዚህ ምንም የለኝ
ጎጆዬ ይሻለኛል ፅዮን እርስት አለኝ
እንግዲ ልመለስ እዚህ ምንም የለኝ
ጎጆዬ ይሻለኛል ፅዮን እርስት አለኝ
እንግዲ ልመለስ እዚህ ምንም የለኝ
ጎጆዬ ይሻለኛል ፅዮን እርስት አለኝ