![Chapter 9 : Eregna](https://source.boomplaymusic.com/group10/M00/02/01/d734663200864e92a84ad4eff9366b2b_464_464.jpg)
Chapter 9 : Eregna Lyrics
- Genre:Alternative
- Year of Release:2024
Lyrics
ትሄድ ትሄድ እና ያን ሁሉ ጎዳና
መኖሯ ይገርማታል ጉዞዋ ሲቃና
በትሩና ዘንጉ ቀርበው እያፅናኗት
እረጅሙንም መንገድ በፍቅር ታምር መሯት
ምድረበዳ ቢወስዳት ትግስት አስተማራት
በለምለሙም መርቶ በፍቅር አሰማራት
በሞት ጥላ አሳልፎ ጽኑ እምነት ሆናት
የእውነት እረኛ በእውነት ጠበቃት
ትለዋለች "እረኛዬ እረኛ እረኛዬ!"
ሰማይዋ ላይ ሰምሮ በአዲስ ኪዳን
ሆነላት ሰንደቅ
ትለዋለች "እረኛዬ እረኛ እረኛዬ!"
አራዊት ቢከባት ይወጣል ቀድሟት
ድል እየሰጣት
በምኞት ተታላ ተቅበዝብዛ እንዳትቀር
ከጥፋት መለሳት በጊቱ እንዳትታደን
ደምግባት ጠፊ ነው ውበት ደግሞ አላፊ
ይሄን ስትረዳ ሆነች ሆደ ሰፊ
ምድረበዳ ቢወስዳት ትግስት አስተማራት
በለምለሙም መርቶ በፍቅር አሰማራት
በሞት ጥላ አሳልፎ ጽኑ እምነት ሆናት
የእውነት እረኛ በእውነት ጠበቃት
ትለዋለች "እረኛዬ እረኛ እረኛዬ!"
ሰማይዋ ላይ ሰምሮ በአዲስ ኪዳን
ሆነላት ሰንደቅ
ትለዋለች "እረኛዬ እረኛ እረኛዬ!"
አራዊት ቢከባት ይወጣል ቀድሟት
ድል እየሰጣት
ለሊት በእሳት አምድ ቀኑን በደመና
ከፊትለፊት ቀድሞ መንገድ እየመራ
በጠሏት በገፏት ሞገስ እየሰጣት
የአባቶቿ እረኛ ከተኩሎች ጠበቃት
ለሊት በእሳት አምድ ቀኑን በደመና
ከፊትለፊት ቀድሞ መንገድ እየመራ
በጠሏት በገፏት ሞገስ እየሰጣት
የአባቶቿ እረኛ ከተኩሎች ጠበቃት
ትለዋለች "እረኛዬ እረኛ እረኛዬ!"
ሰማይዋ ላይ ሰምሮ በአዲስ ኪዳን
ሆነላት ሰንደቅ
ትለዋለች "እረኛዬ እረኛ እረኛዬ!"
አራዊት ቢከባት ይወጣል ቀድሟት
ድል እየሰጣት