
Yedega Sew Lyrics
- Genre:World Music/Folklore
- Year of Release:2024
Lyrics
እጆቼን እሳት ውስጥ ከትቼ ባነድም
ቁርጥምጥም ቁርጥምጥም
ገላህ ሲነካካኝ ሰም ሆኜ ቅልጥ
ትር ትር ድንግጥግጥ
ስሜተ ስሱ ነኝ የዋህ ሰው ቆለኛ
ተራራ አናት ወጣሁ አፍቅሬ ደገኛ
ደመናውን ቁልቁል አዘቅዝቄ እያየው
ፀሐይ ሳትጋረድ ይበርደኛል ምነው
ናልኝ መሞቴ ነው - አሁን ካልታቀፍኩ
ቆለኛ ነኝ እና - ሙቀት የለመድኩ
አያረጅ ስሜትህ - ሸፍኖት በረዶ
እቶናማው ፍቅርህ - እድሜ ልኩን ነዶ
ገላህ ሲነካኝ ነው ከቁር የሚነቁ
የጅ እግር ጣቶቼ የሚነቃነቁ
እሳቱ አቀዝቅዞኝ ሆዴን እንዳባባ
ከንፈሩ እንዴት ሞቀኝ ከደጅ እንደገባ
የደጋ ሰው ፍቅር - የምር የምር
ፍቅር በደጋ ላይ - ስቃይ ስቃይ
የደጋ ሰው ፍቅር - የምር የምር
ፍቅር በደጋ ላይ - ስቃይ ስቃይ
ኮረንቲ እና ትኩስ ለሙቀት አይበቁ
ሲጠጋኝ 'ግላለሁ የገላህ ወበቁ
ብርድ ልብስ በረዶ ብልኮው እራፌ
ተገላልጬ እንኳ 'ሞቃለሁ ታቅፌ
ይነጣሉ እይኖቼ እንደ ፀአዳ አምባ
ዉርጩ ለብለቧቸው ካቀረሩት እምባ
ቀጭ እና ቁርጥማት ቀን እንዳልበረቱ
ስዳበስ ለስልሼ ይሞቃል ሌሊቱ
ገላህ ሲነካኝ ነው ከቁር የሚነቁ
የጅ እግር ጣቶቼ የሚነቃነቁ
እሳቱ አቀዝቅዞኝ ሆዴን እንዳባባ
ከንፈሩ እንዴት ሞቀኝ ከደጅ እንደገባ
የደጋ ሰው ፍቅር - የምር የምር
ፍቅር በደጋ ላይ - ስቃይ ስቃይ
የደጋ ሰው ፍቅር - የምር የምር
ፍቅር በደጋ ላይ - ስቃይ ስቃይ
እጆቼን እሳት ውስጥ ከትቼ ባነድም
ቁርጥምጥም ቁርጥምጥም
ገላህ ሲነካካኝ ሰም ሆኜ ቅልጥ
ትር ትር ድንግጥግጥ
Translate to English