
Mech Temetaleh? Lyrics
- Genre:World Music/Folklore
- Year of Release:2024
Lyrics
Mech Temetaleh? - YEMa
...
ያ'ባ ዉዴ ቃል ማልዶ ቀስቅሶ
በዳኘው ሙሾ የባሰኝ ለቅሶ
መች ትመጣለህ ዘወትር ዜማዬ
አጣኝ ሃሚናው ጠፍቶ አድራሻዬ
መች ትመጣለህ?
እባክህ ባክህ
መች ላግኝህ?
ቆርጠህ መጥተህ
እግሮቼ ዛሉ ሆንኩኝ ደካማ
የቃኘውን ሞት መርዶ እንደሰማ
ተስፋዬ ራደ ወዜ ገረጣ
ካሳን ሆኜያለሁ ገብርዬን ያጣ
መች ትመጣለህ?
ልቤ ከአካሌ ሸሸ ተጣላ
መች ትመጣለህ?
ግርማዬ ካደኝ ሆንኩኝ ነጠላ
መች ትመጣለህ?
ልቤ ከአካሌ ሸሸ ተጣላ
መች ትመጣለህ?
ግርማዬ ካደኝ ሆንኩኝ ነጠላ
አባ ዉዴ አለኝ በሩን አትዝጊ
አንተን ሲያገኝ ነው እኔን ፈላጊ
ደጄን አልዘጋም ባልሆን ብቸኛ
አድራሻዬ ነህ ቋሚ መገኛ
ባይተዋርነት ሆኗል ምርጫዬ
ማን ያገኘኛል ጠፍቶ አድራሻዬ
ልወቀው እና በተስፋ ልስከን
ብትነግረኝ ምነው የትንሳዔን ቀን
መች ትመጣለህ?
ልቤ ከአካሌ ሸሸ ተጣላ
መች ትመጣለህ?
ግርማዬ ካደኝ ሆንኩኝ ነጠላ
መች ትመጣለህ?
ልቤ ከአካሌ ሸሸ ተጣላ
መች ትመጣለህ?
ግርማዬ ካደኝ ሆንኩኝ ነጠላ
መች ትመጣለህ?
እባክህ ባክህ
መች ላግኝህ?
ቆርጠህ መጥተህ
እግሮቼ ዛሉ ሆንኩኝ ደካማ
የቃኘውን ሞት መርዶ እንደሰማ
ተስፋዬ ራደ ወዜ ገረጣ
ካሳን ሆኜያለሁ ገብርዬን ያጣ
መች ትመጣለህ?
ልቤ ከአካሌ ሸሸ ተጣላ
መች ትመጣለህ?
ግርማዬ ካደኝ ሆንኩኝ ነጠላ
መች ትመጣለህ?
ልቤ ከአካሌ ሸሸ ተጣላ
መች ትመጣለህ?
ግርማዬ ካደኝ ሆንኩኝ ነጠላ
ጠፋኝ መፅናኛ ሆንኩኝ አልቃሻ
መምጣትህ ብቻ እምባ ማበሻ
ስጋና ነፍሴን ባቆይ አልዳንኩም
አንተ ከሌለህ እኔም የለሁም
እርግጥ ቢመስለኝ እንደምትመጣ
ቁርጡን ቀን ሳላውቅ ካ'ዘን አልወጣ
ልወቀው እና በተስፋ ልስከን
ብትነግረኝ ምነው የትንሳዔን ቀን
መች ትመጣለህ
ልቤ ከአካሌ ሸሸ ተጣላ
መች ትመጣለህ
ግርማዬ ካደኝ ሆንኩኝ ነጠላ
መች ትመጣለህ
ልቤ ከአካሌ ሸሸ ተጣላ
መች ትመጣለህ
ግርማዬ ካደኝ ሆንኩኝ ነጠላ
እህ እህ እህ
ባይተዋርነት
መች ትመጣለህ
ሆኗል ምርጫዬ
መች ትመጣለህ
ማን ያገኘኛል
መች ትመጣለህ
ጠፍቶ አድራሻዬ
መች ትመጣለህ
ልወቀው እና
መች ትመጣለህ
በተስፋ ልስከን
መች ትመጣለህ
ብትነግረኝ ምነው
መች ትመጣለህ
የትንሳዔን ቀን
መች ትመጣለህ