
Yemenfes tornet Lyrics
- Genre:Hip Hop & Rap
- Year of Release:2023
Lyrics
የመንፈስ ጦርነት
እውነት ከሀሰት የሚቦርቅበት
የመንፈስ ጦርነት
ጨለማ ከብርሃን የሚሞገትበት
የመንፈስ ጦርነት
ነፍስ ከስጋ ጋር የሚቃረንበት
የመንፈስ ጦርነት
ፍጡር በፈጣሪው የሚተብትበት
ቡናችንን ሃሜት የሚል ታርጋ
አብሮነታችንን ማዘናጊያ ማሰናኪያ
የጀግና ታሪካችንን ሸፈንፈን
ባዕድ ጀግና hero ለማዘፈን
Spiderman batman
Ironman ዳሽ ዳሽ
ንጉሱን አስጥለሽ
ነፍጠኛ ያስነሳሽ
ዲሞክራሲ ምናምንት መሪ እያሳጣሽ
ባልቻ ሲባል የአከሌ
ምኒሊክን የአንትና
ዮሃንስን የአከሌ
ቴዎድሮስን የአንትና
ለበዪ ድልድል ሲያመቻቹን
በስርሃት ስም ለስርሃት አልባ ሎሌ ስያዘጋጁን
ችግር አፈታታችን
መኣድ ገበታችን
እርቅ አፈታታችን
በአንድ መቆማችን
ህገ ልቦናችንን
ወግ ስርሃታችንን እምነታችንን
ቁልቁል ለመውረዱ ማነው ጠላታችን ከጉያችን
የመንፈስ ጦርነት
እውነት ከሀሰት የሚቦርቅበት
የመንፈስ ጦርነት
ጨለማ ከብርሃን የሚሞገትበት
የመንፈስ ጦርነት
ነፍስ ከስጋ ጋር የሚቃረንበት
የመንፈስ ጦርነት
ፍጡር በፈጣሪው የሚተብትበት
ተኝተናል ጉድጎድ ሰተውናል
ዝም ብለን ጉዞ ቀጥለናል
የልጅ የእናት አባት ወግ አሳጥተውናል
ባዕድ ጾታ ፀያፍ ሰበከውናል
ሰባዊ መብት በለው ዝቃጭ ሰተውናል
ነፍሳችንን አስጥለው ስጋ ግተውናል
ስርሃቱ ከነፍስ ከእግዜር የመያጣላ
ከእውነት የሚያቃርን ከሰው የሚያባላ
ጋሽ አሌክስ እንዳለው
መገንባት ያለበት ድንጋይ መሪ እየሆነ የተቸገርነው
ሃርንት ልንወጣ ሲገባ ባርንት የገባነው
ትንሳሄ ስንጠብቅ ጨለማን አየነው
ዘውደኛ አባረን ዘረኛ የጫነው
ሹመኛ ሳይሆን አውነት ነው ያጣነው
ጭብል ያጠለቀ ውሪ ነው ያመነው
ቴዎድሮስ ደምህ ደመ-ከልብ ሆኖል
የልጅህ ልጅ ለባርነት ፈቅዶ ታጭቶል
እምዬ ምኒሊክ ድካምህን ምን ይሉታል
በአንዲቶ ኢትዮጵያ ዘረኝነት ፈልቶል
ሀገሬው በሀገሩ ባዳ ነህ ይሉታል
የመንፈስ ጦርነት
እውነት ከሀሰት የሚቦርቅበት
የመንፈስ ጦርነት
ጨለማ ከብርሃን የሚሞገትበት
የመንፈስ ጦርነት
ነፍስ ከስጋ ጋር የሚቃረንበት
የመንፈስ ጦርነት