
Ayleyegn ft. eulmusic Lyrics
- Genre:Hip Hop & Rap
- Year of Release:2023
Lyrics
የልብ ምት ትርታሽን እየሰማው
በትንፋሽሽ እንፋሎት እየሰራው
ሰውንት ሙቀትሽን እየተጋራው
ፊት ዓይን ዓይንሽን እያወራው
እላለው
ፍቅር ነሽ የእኔ አይናማ
የማለዳው ጮራ
ከምንጭ እንደጠራ - ውሃ ውበትን
ሲያሳየኝ ያረፍድና
ቀኑን በዓይኔ ውለሽ
መሽቶም ከእቅፊ ነሽ
ልቤ ግዛትሽ
ፈላጭም ቆራጭም አንቺ
ፈራጄም ወዳጄም አንቺ
ፀባይሽ ወርቅ ነው እንቁ
ስጎዝም ለልቤ ስንቁ
ሲርበኝ ልዩ ፈገግታሽ
ላኪልኝ ፎቶ አንስተሽ
አያስችለኝም እስክደርስ
ከሄድኩበት እስክመለስ
አይለየኝ ከአንችው እቅፍ
አይለየኝ የአንችው ንድፍ
አይለቀኝ ብቀኝ ብፅፍ
ሲከፋሽ እኔው ስፍስፍ
ያመመሽ እኔን ቅስፍስፍ
ታውቂበታለሽ መንከባከቡ
ፍቅር ማላመድ ዜማ ማልበሱን
የልቤ ሙቀት ፀሃይ ብርሃኔ
ጤና-አዳሜ አንቺ ፈውሴ መድህኔ
ጉድ- ምን ብታስነኪኝ - በይ - ህ
ምን ያክል ብታውቂኝ - ቆይ
እንዴት ቢያሳድጉሽ - ድንቅ
አንደበትሽ ያ መካሪዬ
ተረት እንደሚሰማ ህፃን - የሚያቦርቀኝ
ፈገግታሽ ያ አለቃዬ
ከትካዜ ድባቴ ነፃ አውጥቶ - እንደሚለቀኝ
መሃዛ ውበትሽ የአበባ
ታታሪነት ንግስናሽ የንቦ
የማርዎን ያክል ጥፍጥና
አለ በፀባይሽ ውስጥ
የሚታይ ስብህና
አይለየኝ ከአንቺስ አይለየኝ
ጦሜን ባድር - እንቅልፍ ባጣ
ዘመድ ቢሸሽ -ብል- ወገን ባጣ
ከናፍቆትሽ ላይብስ እንዴት ሆኖ
አይለየኝ አሁንም አይለየኝ
አይገርመኝም የጠቢብ ጥበቡ
የምሁር እውቀቱ
ፍቅር ካጣ ቤቱ
አንቺ ነሽ - የመውደድ ፀጋ- ጥበብ ያለሽ - ለእኔ
አንቺው ነሽ - ደምግባት- ሞገስ - ውበት ያለሽ - ለእኔ
አይለየኝ ከአንችው እቅፍ
አይለየኝ የአንችው ንድፍ
አይለቀኝ ብቀኝ ብፅፍ
ሲከፋሽ እኔው ስፍስፍ
ያመመሽ እኔን ቅስፍስፍ