
Tiz alegn ft. eulmusic Lyrics
- Genre:Hip Hop & Rap
- Year of Release:2023
Lyrics
ትዝ አለኝ - ሀገሬ - የጥንቱ - ፍቅራችን
የሽንብራው ጥርጥር የዛፎቹ ፍሬ
የትም የትም ዞሬ
ትዝ አለኝ ሀገሬ
ጥላው ሰፊ ዋርካ የጥበቡ ፍሬ
ውዬ እያደርኩበት ናፈቀኝ ሀገሬ
ትዝ አለኝ - ፍቅር የተሞላ
ያ ደሳሳ ጎጆ
የተስፋዬ ጎጆ
ጠረኑ አይለቀኝም - ቀዬውና ኑሮ
የአብሮነቱ ኑሮ
ጥበብ አስተምሮ
ሀገር አስተምሮ
እንደሩቅ ሀገር ሰው
ከቀዬው እንድራቀ የባዕድ ወገን ሰው
ከሀገሩ ተቀምጦ ሀገር የሚናፍቅ ሀገር የሌለው ሰው
ከዛፉ እንደወደቀ ቅጠል
ከእምነቱ እንደጎደለ መዕመን
ከባህል ከወጉ ከትዝታ ፍቅሩ
ከትውፊት ታሪኩ ተጣልቶ እንደጠፋ
ሆዴ ቦጭ ቦጭ በትዝታ
ሄዶ እንዳይቀር ያ ከፍታ
በአያቱ የኮራው በልጁ ሊረታ
ሀ ሁ ቤት የጥበብ ገበታ
ሀ ሃሎተ እግዚያብሄር
አስራት የቃል ሀገር
ናፈቀኝ
ማን ወሰደው ክብሬን
ግዙፉን መንበሬን
መልሳት ሀገሬን
የሽንብራው ጥርጥር የዛፎቹ ፍሬ
የትም የትም ዞሬ
ትዝ አለኝ ሀገሬ
ጥላው ሰፊ ዋርካ የጥበቡ ፍሬ
ውዬ እያደርኩበት ናፈቀኝ ሀገሬ
ትዝ አለኝ - ፍቅር የተሞላ
ያ ደሳሳ ጎጆ
የተስፋዬ ጎጆ
ጠረኑ አይለቀኝም - ቀዬውና ኑሮ
የአብሮነቱ ኑሮ
ጥበብ አስተምሮ
ሀገር አስተምሮ
የማንነት ጥያቄ - ህ
ማን መሆንን መርሳት - ጉድ
ከትልቁ ዋርካ - በል
አንሶ እንደመረሳት
ሀገሬን - ወገኔን
ያ ደጉ ገበሬን
ህዝቡ ገራገር
ፍቅሩ ባላገር
ወዴት ወዴት ወደዋላ ጉዞ
እንዴት ሊሆን ጥላቻ ተይዞ
ከእጅ ያለ ነገር ርቆ
እንዴት ይናፈቅ ትዝታ ጠምቆ
ልሁል በገዛ ሀገሩ አይከበርም
ባርነት ያላየ ነፃነት አያውቅም
በስራ የከበረ በወሬ አያፍርም
ትልቅ ሆኖ ያወቀ
ትንሽ ሆኖ አይቀርም
የሽንብራው ጥርጥር የዛፎቹ ፍሬ
የትም የትም ዞሬ
ትዝ አለኝ ሀገሬ
ጥላው ሰፊ ዋርካ የጥበቡ ፍሬ
ውዬ እያደርኩበት ናፈቀኝ ሀገሬ
ትዝ አለኝ - ፍቅር የተሞላ
ያ ደሳሳ ጎጆ
የተስፋዬ ጎጆ
ጠረኑ አይለቀኝም - ቀዬውና ኑሮ
የአብሮነቱ ኑሮ
ጥበብ አስተምሮ
ሀገር አስተምሮ