Liyu Hono Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2024
Lyrics
የሰማያት ውበት በሱ አይደለም ወይ
ሳይለዋውጥ መልኩን እስካሁን የሚታይ
ከቶ እሱን የሚመስል ከፍጥረታት ዓለም
በኃይል ቢሆን በክብር አንድም ወገን የለም
ልዩ ሆኖ ይኖራል
ከሱ ጋራ ማን ይስተያያል
ባህሪው ልዩ ነው ከሰው ሁሉ
በሱ መኖር ሁሉም ይኖራሉ
ልዩ ሆኖ ይኖራል
ከሱ ጋራ ማን ይስተያያል
ባህሪው ልዩ ነው ከሰው ሁሉ
በሱ መኖር ሁሉም ይኖራሉ
ጥላ የለበትም የአካሉ ብርሃን መልኩ ተውቦና ደምቆ
የህልውናው ስፋት ወሰን ገደብ የለው ከዓለም ጠቢባኖች በዕውቀት ልቆ
የአሸዋውን ሥፍር የኮከብን ብዛት በቁጥር ያውቀዋል
የበረዶን ክምር ተራራ አድርጎ እርሱ ያኖረዋል
ልዩ ሆኖ ይኖራል
ከሱ ጋራ ማን ይስተያያል
ባህሪው ልዩ ነው ከሰው ሁሉ
በሱ መኖር ሁሉም ይኖራሉ
በጋና ክረምቱን በጊዜ በወራት በምድር ሁሉ ላይ ያዛል
ፐልያዲስ ኦርዮን ድብ የተባለውን ከዋክብት በሰማይ እንዲታይ አድርጓል
የምድርንም ስፋት ባሕርና የብሱን ይዞ በመዳፉ
ሉዓላዊ ጌታ ስለሆነ እርሱ ፍጥረታት አረፉ
ልዩ ሆኖ ይኖራል
ከሱ ጋራ ማን ይስተያያል
ባህሪው ልዩ ነው ከሰው ሁሉ
በሱ መኖር ሁሉም ይኖራሉ
የሰማያት ውበት በሱ አይደለም ወይ
ሳይለዋውጥ መልኩን እስካሁን የሚታይ
ከቶ እሱን የሚመስል ከፍጥረታት ዓለም
በኃይል ቢሆን በክብር አንድም ወገን የለም
ልዩ ሆኖ ይኖራል
ከሱ ጋራ ማን ይስተያያል
ባህሪው ልዩ ነው ከሰው ሁሉ
በሱ መኖር ሁሉም ይኖራሉ
ልዩ ሆኖ ይኖራል
ከሱ ጋራ ማን ይስተያያል
ባህሪው ልዩ ነው ከሰው ሁሉ
በሱ መኖር ሁሉም ይኖራሉ