![Misgana ft. Biniyam Desalegn](https://source.boomplaymusic.com/group10/M00/06/11/4624f189736547a398851da394f0a082_464_464.jpg)
Misgana ft. Biniyam Desalegn Lyrics
- Genre:Hip Hop & Rap
- Year of Release:2021
Lyrics
አታየኝም ወይ አትሰማኝም ወይ ለምን ትላለህ
ችግር እያለ ክፉ እያየለ ለምን ላመስግን ለምን ትላለህ
አታየኝም ወይ አትሰማኝም ወይ ለምን ትላለህ
ችግር እያለ ክፉ እያየለ ለምን ላመስግን ለምን ትላለህ
ሁለት ጥያቄ፤
አጉረምርመህ መልስ አገኘህ? እ?
እግዜሩንስ ወቅሰህ ከጭንቀት አረፍክ?
ጠቢብ ለመሆን ከሰነፍ ተማር
አመስግን እንጂ ፍፁም አታማር
እንዳይሆንብህ
ለልብህ ህመም ለጨጓራህ ቃር
የምሬትን ቃል አርቅ ካንተ ጋር
ማን ክፉን ያመጣል ከውሸት አባት ሌላ
አባቴ እንደሆነ የለው የክፋት ጎተራ
ለኔ የሚራራ፤ በጎ ስጦታና ፍፁም በረከት ነው ሁሌ የሱ ስራ
ደስታና ሰላም ከውጭ አይመጣም
የገንዘብ ብዛት እረፍት አይሰጥም
የለኝም አትበል የሌለህ የለም
እግዚአብሄር ካለህ የጎደለህ የለም
አመስግንና መፍትሄው ይገለጥ
'ምታርፍበት ሰላም ከችግርህ ይብለጥ
የምስጋናን ነዶ እወዘውዛለሁ
እንደሰባ እንቦሳ በፊቱ ዘላለሁ
ክብር ይገባዋል ሀሌሉያ እላለሁ
ነፍሴ ታሠስግንህ እሰግድሀለሀሁ
እረካሁ ተደሰትኩ ስል ሰይጣን በጆሮዬ
ምን ኖሮህ ማን ሆነህ ይላል እንዳብድ ጨርቄን ጥዬ
የሌለኝ ያልሆንኩት ደስታን አይሰጠኝም
የአምላክ ልጅ ከመሆን የሚበልጥ ደስታ የለም
ደስታና ሰላም በውስጤ አለ
ለምን ላጉረምርም አባቴ ከኔጋ እያለ
ላመስግን ዝም ብዬ ተመስገን ብዬ
ያኔ ሁሉ ይቀላል አልኖር ታግዬ
እንዴት እንደሚቀደም ከሰው ሳይጋፉ
ገብቶኛል ዘንድሮ የበረከት ቁልፉ
እንዴት እንደሚቀደም ከሰው ሳይጋፉ
ገብቶኛል ዘንድሮ የበረከት ቁልፉ
በምስጋና በውዳሴ ቀኑን ካልገፉ
በረሀ ላይ መሞት ነው የማጉረምረም ትርፉ
በምስጋና በውዳሴ ቀኑን ካልገፉ
በረሀ ላይ መሞት ነው የማጉረምረም ትርፉ