ይብዛልኝ መታዘዜ Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2024
Lyrics
ግራ ቀኜን ላንተ ትጉህ አድርገው
ቀንሳለ ልሩጥህ መንግስትህን ላስፋው
ደጆቼ ተከፍተው ብርሃኔም በርቶ
የመንግስትህ ጉዳይ ያጥምደኝ በዝቶ
ይብዛልኝ መታዘዜ
ይብዛልኝ ላንተ መሮጤ
ይብዛልኝ የመንግስትህ ጉዳይ
ይክበደኝ ከሌላው በላይ
ኢያኤል ያቺ ሴት ግራዋም ቀኟም ታዛዥ
በድንኳን ከሚኖሩ ከሴቶች ይልቅ የተለየች
ውሀ ለለመነ ወተት ሰጪ በከበረ ዳካ
ሲሳራን የዘረረችው በእግሯ ስር አጋድማ
ግራዋን ለካስማ ቀኝ እጇን ለመዶሻ
በጥበብ የተሞላች ጠላትን የዘረረች
የሆነች ታታሪ ለመንግስትህ ሰሪ
የሆነች ሰራተኛ ለስራህ የማትተኛ
ግራ ቀኜን ላንተ ትጉህ አድርገው
ቀንሳለ ልሩጥህ መንግስትህን ላስፋው
ደጆቼ ተከፍተው ብርሃኔም በርቶ
የመንግስትህ ጉዳይ ያጥምደኝ በዝቶ
ይብዛልኝ መታዘዜ
ይብዛልኝ ላንተ መሮጤ
ይብዛልኝ የመንግስትህ ጉዳይ
ይክበደኝ ከሌላው በላይ
በችግር በመከራ በፅናት ወንጌል ሰባኪ
በድንጋይ ተወግሮ ማልዶ ለወንጌል ዘማች
ግርፋት ደዌ ማያስቆመው በዕፉኝት መነደፍ
እለት እለት ሚያሳስበው የመንግስትህ መስፋት
ሁልጊዜ ደስ የሚለው ታስሮ እንኳን የማይከፋው
እንደ ጳውሎስ የጀገነ እስከ ሞት የቆረጠ
የሆነ ሰራተኛ ለወንጌል የማይተኛ
የሆነ ታታሪ የመንግስትህ ሎሌ
በዚህች አጭር እድሜ መላኬን ዘንግቼ
ለራሴ ጉዳይ እንዳይሆን ሩጫዬ
ከእናቴ ማህፀን ጀምሮ ሲለየኝ የኔ ብሎ
እሮጣለሁኝ ከስጋ ከደም አልማከርም
እሮጣለሁኝ ከስጋ ከደም አልማከርም
ይብዛልኝ መታዘዜ
ይብዛልኝ ላንተ መሮጤ
ይብዛልኝ የመንግስትህ ጉዳይ
ይክበደኝ ከሌላው በላይ