
ይኑርልን ጌታ Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2024
Lyrics
ያደርንበት ኃጢአት ከንስሃ ጣፍጦ
እግዚአብሔርን መፍራት ተንቋል አመፅ በዝቶ
አንዳችን በኃጢአት ከሌላው ለመላቅ
ተፎካከርን ጌታን ከቤቱ ለማራቅ
ያደርንበት ኃጢአት ከንስሃ ጣፍጦ
እግዚአብሔርን መፍራት ተንቋል አመፅ በዝቶ
አንዳችን በኃጢአት ከሌላው ለመላቅ
ተፎካከርን ጌታን ከቤቱ ለማራቅ
አይታገልም ጌታ ከአፍኒንና
ከፊንሃስ ጋራ
ይርቃል እንጂ ከማይፈሩት
ትራፊ እየሰጡ ከሚንቁት
ኢካቦድ ሆኖ በሐገሪቱ
በእልልታ ቢቀለጥ መንደሩ
አደንድኗል አመፅ ልባቸውን
እስኪሰጥ በጅራፍ ዋጋቸውን
ና.. ባደባባይ ስምህ ተሰድቧል
ና ና መልሰን ፊትህ ወድቀናል
ና.... የተወሰደው ክብር ይመለስ
ና ና አንተ ቆይልን ሚሄደው ይሂድ
ሙሽራው እያለ ሎሌው ደምቆ
ነውር የማይፈራ ምህረቱን ተለማምዶ
ሙሽሪትም ደጇን ለሌላው ከፍታ
በአላፊው አግዳሚው ጨረሰች ዘይቷን
የለበትም ጌታ በምስባኩ
በተዘጋዘጀው በስሙ
ይሰበካል እንጂ የሰው ዝና
ባሪያው ከጌታው ልቋልና
አይጠራም ኢየሱስ በመድረኩ
አይነገርም ከቶ ትምህርቱ
ይሰበካል እንጂ ታምራቱ
ለንግድ የሚሆን ጥራዝ ጥቅሱ
ይኑርልን ጌታ በቤቱ
ይሰንብት ለርስቱ
ሚፈልገው አለ ከነፍሱ
የማይኖር ያለ እሱ
ባይተዋር አናርገው አንግፋው
ይኑርልን ጌታ
ዝም ማለቱን አንናቅ
ምህረቱ ሲበዛ
ላይ ላያችን ሲታይ ጣዖት ተፀያፊ
በቤተ መቅደስ ግን ከእግዜር እጅ ዘራፊ
በድፍረት ልምምድ ጌታን ስንጋፋ
የምህረት ደጁን እግዜር እንዳይዘጋ
ና.. ባደባባይ ስምህ ተሰድቧል
ና ና መልሰን ፊትህ ወድቀናል
ና.... የተወሰደው ክብር ይመለስ
ና ና አንተ ቆይልን ሚሄድዉ ይሂድ