
Chapter 7 : Menged Lyrics
- Genre:Alternative
- Year of Release:2024
Lyrics
ተንከራተተች ነፍሴ ላይ ታች እያለች
መውጣትን እያየች መውረድን ተማረች
ምርኩዙን ብታገኝ እሚያደርሳትን እሩቅ
በበትሩም ፀናች አደረጋት ትሁት
ቢመሰክር መብረቅ በድምፅ አልባ ጩኸት
ላይደርስላት ታያት አደረጋት መንገድ
ገደል ሆኛለው አምባን አይቼ
ቆላ ሄጃለው ደጋን ፈርቼ
ጉድጓድ ወርጄ አየሁኝ ዳገት
እንዴት ልድረስ ቀረው መንገድ
መጨረሻም የለው የነቃ ሰው ቅዠት
ቢጠሩት አይሰማም አውቆ ከተኛበት
እረኛ ያጣ ቀን ጠቦት ይታደናል
በሞት ጥላ ቢሄድም ፍርሃት ይገድለዋል
ቢመሰክር መብረቅ በድምፅ አልባ ጩኸት
ላይደርስላት ታያት አደረጋት መንገድ
ገደል ሆኛለው አምባን አይቼ
ቆላ ሄጃለው ደጋን ፈርቼ
ጉድጓድ ወርጄ አየሁኝ ዳገት
እንዴት ልድረስ ቀረው መንገድ
አፈር ቢመስለው የቆመ ብቻውን
"መንገድ" ልሁን ቢል በጋ በጋውን
ዝናብ እያካፋ ሲመጣ ከላይ
ድጥ ያደርገዋል መድረሻው ላይታይ
ተይ ነፍሴ እባክሽ አትለይኝ ከፍጥረት
ባይገባሽ ሕይወቱ መኖሩ በስደት
እንደው ብጠፋ ያቺ የእውነት ሕይወት
ቃል ስጋ ለብሶ ይሆነናል መንገድ