![Maderiyah](https://source.boomplaymusic.com/group10/M00/05/24/1a2779297497417ca66073d8f20730e4_464_464.jpg)
Maderiyah Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2023
Lyrics
ልቤን ላንተ የሚመች አርገው
እኔነቴ እኮ ያንተ ነው
መኖሪያ ቤትህ ማደሪያ እኮ ነው/3/
ቤተመቅደስህ ማደሪያ እኮ ነው
እንዳይያዝ ልቤ በሌላ ነገር
እንዳያይ አይኔ ካንተ በስተቀር
ኮትኩተህ ተክለህ ያንተ የሆነዉን
እንድታውቅ አርጋት ነፍሴን ሰማያዊውን
ያንተ ያልሆነውን ጥረግ ከውስጤ
አንጻኝ እጠበኝ ያንተው ነኝ ውዴ
አንተ የምትከብርበት ይሁን መንገዴ
አንተን ብቻ መፈለግ ይሁን ልማዴ
ልቤን ላንተ የሚመች አርገው
እኔነቴ እኮ ያንተ ነው
መኖሪያ ቤትህ ማደሪያ እኮ ነው/3/
ቤተመቅደስህ ማደሪያ እኮ ነው
ፈቃድህ ፈቃዴ መሻትህ መሻቴ
ልሁን እንደልብህ አትተወኝ ለራሴ
በህይወቴ ዘመን ይህንን እሻለው
ቅዱሱ መንፈስህ ልቤን ይመርምረው
አንተን ንጉሴን አንድ ቀን እስካይ
ጊዜዬ ደርሶ እስክንገናኝ
እጅህ እንዳይለቀኝ ይሁን ምርኩዜ
አጥብቀህ ያዘኝ ሁን መጨረሻዬ
ልቤን ላንተ የሚመች አርገው
እኔነቴ እኮ ያንተ ነው
መኖሪያ ቤትህ ማደሪያ እኮ ነው/3/
ቤተመቅደስህ ማደሪያ እኮ ነው
ክፉው ቀን ሲመጣ ልቤ እንዳይሸነፍ
ተረትቶ በከንቱ በአለም እንዳይጠለፍ
የጦር እቃህን ይልበሰ ቃልህ ይቀረፅበት
ይሸሸግ በአንተ የበላይ ሁንለት
ዝቅ ይበል ለአምላኩ ጠብቀው እንዳይኮራ
እንዳይርቅህ አንተን ጌታ ሆይ አደራ
ይታዛዝ ይገዛ ላንተ ይሸነፍልህ
ያንተ ላንተ ብቻ እንዳልከው ይሁንልህ
ልቤን ላንተ የሚመች አርገው
እኔነቴ እኮ ያንተ ነው
መኖሪያ ቤትህ ማደሪያ እኮ ነው/3/
ቤተመቅደስህ ማደሪያ እኮ ነው