![Abate Neh](https://source.boomplaymusic.com/group10/M00/05/24/1a2779297497417ca66073d8f20730e4_464_464.jpg)
Abate Neh Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2023
Lyrics
ከልጅነቴ አቅፈህ አባብለህ
አሳደከኝ በክንድህ ደግፈህ
ፈጥኖ ደራሽ ስጠራህም አቤት ምትለኝ
ከተፍ የምትል ሁልጊዜ ምትረዳኝ
ገና ሳልነግርህ ውስጤን ታውቃለህ
አንተ እኮ አባቴ ነህ
አንተ እኮ ወዳጄ ነህ
አንተ እኮ አባቴ ነህ
ከማንም በላይ ወዳጄ ነህ
አንተ እኮ አባቴ ነህ
ማን እንዳንተ ማን እንዳንተ
ስንቱን አለፍኩኝ ባንተ /2/
አንተ ብቻ ቅርብ ለልቤ
አንተ ብቻ የዘላለሜ
አንተ ብቻ ቅርብ ለልቤ
አንተ ብቻ ነህ የዘላለሜ
ከእስትንፋሴ በላይ የምትቀርበኝ
እንደ አንተ እኔ ማንም የለኝ
ህይወቴ የተያዘው ባንተ
ያንተ ጥገኛ ነኝ ያንተ
ማን እንዳንተ ማን እንዳንተ
ስንቱን አለፍኩኝ ባንተ /2/
አንተ ብቻ ቅርብ ለልቤ
አንተ ብቻ የዘላለሜ
አንተ ብቻ ቅርብ ለልቤ
አንተ ብቻ ነህ የዘላለሜ
ጉልበትህ የማይዝል የማይታክት
ሰለቸኝ አታውቅም እኔን ስታግዝ
ስትረዳኝ ሳትለይ ከጎኔ
አይቼሃለሁኝ በዘመኔ
ዘንድሮም ተስፋ ነህ ለልቤ
ኃይልህ እየተገለጠ በድካሜ
ማነው ያበሰልኝ እንባዬን
ማነው ያጽናናኝ በጓዳዬ
ማነው ሳይሰለች የሚሰማኝ
እግዚአብሄር እንዳንተ ማንም የለኝ
ለማነው ሚስጥሬን የማዋየው
ለማነው የልቤን የምነግረው
ለማነው ጥያቄዬን የማቀርበው
እግዚአብሄር ለአንተ ብቻ ነው