![Eyesus](https://source.boomplaymusic.com/group10/M00/05/24/1a2779297497417ca66073d8f20730e4_464_464.jpg)
Eyesus Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2023
Lyrics
የእግዚአብሄር ልጅ ኢየሱስ /ኢየሱስ/
ቤዛ የሆንከኝ ኢየሱስ /ኢየሱስ/
ውለታህ ብዙ ኢየሱስ /ኢየሱስ/
ምን ልክፈልህ ኢየሱስ /ኢየሱስ/
እሾህ በራስህ ግርፍያና ቁስልህ አላስቆመህም
ለሰቀሉህም ይቅር በላቸው እንጂ ሌላን አላልክም
ፍቅር በልጦብህ ኃጢያትን ለብሰህ እኔን እያሰብክ
ሁሉንም ችለህ የሰማዩን አምላክ አባትህን ታዘዝክ
ቃሉ እስኪፈጸም አንተ የጌቶች ጌታ ስጋን ለብሰህ
ተከተሉኝ አልከን ስራህን ፈጽመህ ድልን ነስተህ
ዛሬን አየሁ ባንተ ሰው ላረከኝ ጌታ ልዘምርልህ
ስለሚገባህ ላንተ ለመድኃኒቴ ልስገድልህ
የእግዚአብሄር ልጅ ኢየሱስ /ኢየሱስ/
ቤዛ የሆንከኝ ኢየሱስ /ኢየሱስ/
ውለታህ ብዙ ኢየሱስ /ኢየሱስ/
ምን ልክፈልህ ኢየሱስ /ኢየሱስ/
ከቶ አይቀልብኝ በቀራኒዮ መስቀል የሆንከው ስለኔ
አፈ-ታሪክ ወይ ከንቱ ተረት አይደለም መዳኔ
አይታያት ሌላ ነፍሴ ተማርካ በጥልቅ ፍቅርህ
ላንተ ብቻ ልቤ ተገዝቷል አይችልም ሊለይህ
እኔ ዝቅ ብዬ አንተን እያሳየሁ መኖር እሻለው
ዝም የማያሰኝ ስለ ኢየሱሴ አለኝ የምለው
የዘላለም ንጉስ አልፋ ኦሜጋው እውነት ህይወት መንገድ ነው
ቀሪ ዘመኔን እመሰክራለሁ ኢየሱስ ጌታ ነው
የእግዚአብሄር ልጅ ኢየሱስ /ኢየሱስ/
ቤዛ የሆንከኝ ኢየሱስ /ኢየሱስ/
ውለታህ ብዙ ኢየሱስ /ኢየሱስ/
ምን ልክፈልህ ኢየሱስ /ኢየሱስ/