![Megegnetih](https://source.boomplaymusic.com/group10/M00/05/24/1a2779297497417ca66073d8f20730e4_464_464.jpg)
Megegnetih Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2023
Lyrics
የፈለጉኝ ያገኙኛል ያልክ
ማንንም አልከለከልክ
ሃብታም ደሃም ብለህ አታዉቅ
ሁሌም ቅርብ ለናፈቀክ
ስለዚህ ሌላውን ሁሉ ንቄ አለሁ በፊትህ
መገኘትህ ያግኘኝ ልሞላ በመንፈስህ
ልብን የምታውቅ የምትመረምር
አንድም የለም በፊትህ ስውር
አንደበትን አልፈህ ታያለህ
በእውነት የሚሹህንም ታውቃለህ
የተራቆተውን ማንነቴን ይኸውና በፊትህ
ነፍሴ ተጠምታህ አለች አንተን ነው የምትፈልግህ
የፈለጉኝ ያገኙኛል ያልክ
ማንንም አልከለከልክ
ሃብታም ደሃም ብለህ አታዉቅ
ሁሌም ቅርብ ለናፈቀክ
ስለዚህ ሌላውን ሁሉ ንቄ አለሁ በፊትህ
መገኘትህ ያግኘኝ ልሞላ በመንፈስህ
በእውነት በመንፈስ ሆኜ ይህን ነው የምለምንህ
መገኘትህ ያግኘኝ ልሞላ በክብርህ
የፈለጉኝ ያገኙኛል ያልክ
ማንንም አልከለከልክ
ሃብታም ደሃም ብለህ አታዉቅ
ሁሌም ቅርብ ለናፈቀክ
ስለዚህ ሌላውን ሁሉ ንቄ አለሁ በፊትህ
መገኘትህ ያግኘኝ ልሞላ በመንፈስህ
ነፍሴ ታደንቅሃለች እጅጉን ወዳሃለች
ቃልህ ህይወት ሆኗታል ባንተ ትረጋጋለች
ነፍሴ ታደንቅሃለች እጅጉን ወዳሃለች
መልካሙን እድል መርጣ በእግርህ ስር ትገኛለች
የሩቅ አይደለህም ከእኔ ጋራ ነህ
የሩቅ አይደለህም በዉስጤ አለህ
የሩቅ አይደለህም ከእኔ ጋራ ነህ
የሩቅ አይደለህም በውስጤ ያለህ
የሩቅ አይደለህም ከእኔ ጋራ ነህ
የሩቅ አይደለህም በእኔ ዉስጥ አለህ
የሩቅ አይደለህም ከእኔ ጋራ ነህ
የሩቅ አይደለህም በውስጤ ያለህ